2009-11-25 14:08:59

የቤተሰብ መበታተን ምክንያት


ለአቅመ አዳም ያልደረሱት የኅብረተሰብ አባላትን የሚንከባከብ መተር የተሰኘው የግበረ ሰናይ ማኅበር፣ በቤተሰብ ውስጥ የሚፈጸመው የወሲብ በደል እጅግ ከፍ እያለ መሆኑ በመግለጥ፣ በቤተሰብ ዘንድ የሚፈጠረው ችግር እና RealAudioMP3 አለ መግባባት ብሎም የሚከሰተው ቀውስ የቤተሰብ አባላትን ለተለያዩ ሰብአዊ ማኅበራዊ እና ኤኮኖሚያዊ ችግር የሚያጋልጥ ብቻ ሳይሆን፣ ይህ ዓይነቱ የቤተሰብ መቃወስ ሕጻናት ለዘርፈ ብዙ ችግሮች የሚያጋፍጥ እና ለወሲብ በደል ሰለባ እንደሚያደርግ ሜተር የሰጠው መገልጫ ያመለክታል።

የዚህ የግብረ ሰናይ ማኅበር ሊቀ መንበር ኣባ ፎርቱናቶ ዲ ኖቶ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ በአለማችን በሕጻናት ላይ የሚፈጸመው የወሲብ በደል እጅግ እየተስፋፋ እንዳውም የተራቀቀው የቴክኖሎጂ ግኝቶችን በመጠቀም ሕጻናት ልክ በሱቅ ለሽያጭ እንደሚቀርብ ቁሳቁስ ሆነው በተለያዩ የወንጀል ቡድኖች ለወሲብ በደል ተጋልጠው ይገኛሉ፣ የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት ጉዳይ በተመለከተ ያተጠናቀረው ሰነድ በመጥቀስ ኣባ ዲ ኖቶ ይላሉ፣ በዓመት ውስጥ 200 ሺሕ ሕጻናት የወሲብ በደል ሰለባ እንደሚሆኑ በመግለጥ በሳቸው የሚመራው የሕጻናት ጉዳይ የሚንከባከበው ማኅበር 10 ሺሕ የተለያዩ ድረ ገጾች ሕጻናትን ለወሲብ አደጋ የሚያጋልጡ መሆናቸው ለሚመለከተው አካል በማሳወቅ ክስ እንዳቀረበም ገልጠው፣ ሕጻናት ለዚህ ጸያፍ ተግባር ሰለባ ሆነው ማየቱ እጅግ የሚዘገንን ነው ብለዋል።

የተረጋጋ እና ሚዛኑ ለጠበቀ ማኅበረሰብ መሠረት ቤተ ሰብ ነው፣ ስለዚህ ቤተ ሰብ የሕንጸት ማእከል መሆኑ ተዘንግቶ በቤተሰብ አባላት ዘንድ የአብነት መቃወስ አንሰራፍቶ እየተስፋፋ ባለው የወሴብ ስሜት ብቻ የሚከተል ኢሞራላዊው ባህል ተግባር እንደ ልሙድ እና ተራ ተግባር ሆኖ ማየቱ እጅግ የሚዘገንን ነው፣ ስለዚህ ቤተሰብ የሕንጻት ማእከልነቱ ዳግም ማረጋገጥ ይኖርበታል ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.