2009-11-25 14:06:54

የስነ ምግባር ቅጥ በኤኮኖሚው ዓለም


እ.ኤ.አ. በ 2005 ዓ.ም. እዚህ በሮማ የስነ ሕግ፣ የስነ ኤኮኖሚ፣ የስነ ታሪክ እና የተግባረ እድ ዘርፎች በማካተት የተመሠረተው የኤውሮጳ መንበረ ጥበብ ከትላትና በስትያ የዘንድሮ የትምህርት ዓመት መባቻ የቅድስት RealAudioMP3 መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶኔ ወደ አዲስ ሰብአዊነት በሚል ርእስ ሥር በሰጡት ሥልጣናዊ ትምህርተ ንባብ በይፋ ተከብረዋል።

የትምህርት መባቻ ምክንያት በተካሄደው ጉባኤ የመንበረ ጥበቡ ዋና አስተዳዳሪ ኣባ ፓውሎ ስካራፎኒ ባሰሙት ንግግር ተጀምሮ የኢጣሊያ የኤኮኖሚ ሚኒ. ጁሊዮ ትረሞንቲ ዓለም አቀፍ የኤኮኖሚ ቀውስ ወዲህ በሚል ርእስ ሥር በሰጡት አስተምህሮ ተፈጽሟል።

ብፁዕ ካርዲናል በርቶኔ አዲስ ሰብአዊነት ጉዳይ የቤተክርስትያን ሥልጣናዊ ትምህርት የሚሰጠው ጥልቅ እና ሰፊ ትንታኔ በማስረዳት፣ በአሁኑ ወቅት የሰው ልጅ ሰብአዊ ክብሩ እና ኃላፊነቱን ዳግም ለማቀዳጀት የሚያችል አዲስ ሰብአዊነት ማረጋገጥ ይቻላልን፣ ብለው ጥያቄ በማቅረብ፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ፍቅር በሐቅ በሚል ርእስ ሥር የደረስዋት ዓዋዲት መልክት ዋቢ በማድረግ ብጹዕነታቸው የኤውሮጳ ኤኮኖሚያዊ ጉዳይ በመዳሰስ ዓለማዊ ትሥሥር፣ የነጻው ርእዮት፣ ስነ ቁጠባዊ መስፋፋት፣ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ግኝቶች፣ የሰው ልጅ ጸአት፣ እየተስፋፋ ያለው የማህበዊ ሕይወት መዛባት እና አልቦ እኩልነት፣ ማንነትህን ለማረጋገጥ በሚል ዓላማ የሚከሰቱት ግጭቶች እና በተፈጥሮ አካባቢ እና በአየር ንብረት ላይ የሚፈጸመው በደል በመዘርዘር፣ እነዚህ ሁሉ የዘረዘሩዋቸው ነጥቦች እና እንዲሁም በዓለማችን ተከስቶ ያለው የኤኮኖሚ ቀውስ በዓለማችን አዲስ ሰብአዊነት እንዲጸና የሚያሳስብ ጉዳይ ነው ብለዋል።

የተከሰተው የኤኮኖሚ ቀውስ የኤኮኖሚ መዋቅሮች ያለባቸው ግድፈት የሚያመለክት ሲሆን፣ የዚህ ሁሉ መሠረት ደግሞ የኤኮኖሚው ሂደት ስነ ምግባራዊ ቅጥ አልቦ በመሆኑ ነው፣ ስለዚህ የኤኮኖሚው ዓለም የሚከተለው የስነ ምግባር ቅጥ እጅግ አስፈላጊ ነው ብለዋል። አክለውም ከ 1970ዎች ዓመተ ምህርተ ወዲህ በምዕራቡ ዓለም የኤኮኖሚው ሂደት እጅግ የሚደነቅ እና አርኪ ውጤት በመስጠቱ ምክንያት ይህ ምዕራባዊው የኤኮኖሚው ስልት፣ ባህል ተደርጎ በሁሉም አገሮች ተሰራጭቶ የአመርቂ ኤኮኖሚ መመዘኛ ሆኖ ይባስ የኤኮኖሚው ጉዳይ ፍጻሜ የመኮነን እና የማጽደቅ ብቃት ያለው መመዘኛ ተደርጎ በመታየቱ ምክንያት፣ በአሁኑ ወቅት በዓለማችን ያስከተለው የኤኮኖሚ ችግር ለማንም የተሰወረ አይደለም፣ ስለዚህ የኤኮኖሚው ጉዳይ የሚመለከት የስነ ምግባር ቅጥ እጅግ ወሳኝ ነው ብለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.