2009-11-25 14:16:47

ሶማሊያ


በሶማሊያ ያለው የሰብአዊ ቀውስ እጅግ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱ ሲገለጥ፣ ሶማሊያ ከኢትዮጵያ በሚያዋስናት የቤለድውይነ ክልል እጅግ የከፋ መሆኑ ኢርነ የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት አቀነባበሪ ጽ/ቤት RealAudioMP3 የዜና አገልግሎት በመጥቀስ፣ በአል ሸባብ እና በሶማሊያው የሽግግር መንግሥት የመከላከያ ኃይል መካከል ያለው እልባት ያጣው ግጭት መላውን የሶማሊያ ሕዝብ ለከፋ አደጋ እያጋለጠ፣ የሰብአዊው ችግር ከቀን ወደ ቀን እያባባሰው መሆኑ ያመለክታል።

በቤሌድወይነ ክልል ያለው ውጥረት 15 ሺሕ የክልሉ ሕዝብ ለመፈናቀል አደጋ በማጋለጡ ምክንያት ህዝቡ በመጠለያ ሰፈር ያለ ቢሆንም ቅሉ፣ በክልሉ ያለው የሰብአዊው ችግር እጅግ የከፋ መሆኑ ሚስና የዜና አገልግሎት ይጠቁማል።

ለከፋው የሰብአዊ አደጋ የተጋለጠው የሶማሊያው ሕዝብ የሚቀርብለት የሰብአዊ እርዳታ በቂ እንዳልሆነ ኢሪን በማሳወቅ፣ በግጭቱ ሳቢያ ከተሞች የሚቆጣጠሩት ታጣቂ ኃይሎች በየጊዜው የሚለዋወጡ በመሆናቸውም ምክንያታ ሕዝቡ በተደጋጋሚ ለመፈናቀል አደጋ ከማጋለጡም ባሻገር ለሚቀርብለት የሰብአዊ እርዳታ እንቅፋት መሆኑም የዜናው አገልግሎት ያረጋገጣል።

ዓለም አቀፍ የምግብ ድርጅት በሶማሊያ የተፈናቀለው ሕዝብ ብዛት ሶስት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሺህ መሆናቸው እና ይህ ሕዝብ ለመርዳት የሚደረገው የሰብአዊ እርዳታ እቅድ በክልሉ ባሉት ግጭቶች ሳቢያ በተለያየ ወቅት ሲሰናከል፣ የሰብአዊ እርዳታ አቅራቢ ድርጅት ሰራተኞች ሕይወት ለአደጋ እያጋለጠ ሲሆን፣ በክልል የነበሩት 12 የዓለም አቀፍ የምግብ ድርጅት ሰራተኞች በክልሉ ባለው የጸጥታ እና የደህነንት ችግር ሳቢያ ከተማይቱን ለቀው ለመውጣት መገደዳቸው ድርጅቱ አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.