2009-11-24 12:35:31

ክርስቶስ በፍቅር የሚገዛ ንጉሥ ነው


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ትናንት እሁድ እኩለ ቀን የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ከመምራታቸው በፊት ባሰሙት መንፈሳዊ መልእክት ክርስቶስ ራሱን በሌሎች ላይ በማስገደድ ወይም ጫና በማውረድ ሳይሆን፣ RealAudioMP3 የሰው ነፃነት የሚያከብር ፍቅር የሚገዛ ንጉሥ ነው ሲሉ ኣረጋገጡ።

ቅዱስነታቸው ይህን የገለጡት ዕለቱ ክርስቶስ ንጉሥ የሚከበርበት እሁድ በመኖሩ ነው። ቅዱስነታቸው መልእክታቸውን በማስፋፋት፣ የክርስቶስ ንጉሥነት በዓለም ላይ እንደምናየው የታላላቅ ነገሥታት ዓይነት ኣይደለም፣ ንጉሥነቱ ኃጢኣት እና ሞት አሸንፎ በደነደኑ ልቦችም ሳይቀር ተስፋን የሚያነቃቃ ኃይል እና ሥልጣን ነው።

የክርስቶስ ሥልጣን ወይም ኃይል የሞትን ግዛት አሸንፎ ከኃጢአት ባርነት ነፃ የሚያወጣ ዘለዓለማዊ ሕይወት የሚሰጥ መለኮታዊ ሥልጣን ነው። …








All the contents on this site are copyrighted ©.