2009-11-23 15:29:31

ዴሞክራሲያዊት ሬፓብሊክ ኮንጎ


ባለፈው ወር በዴሞክራሲያዊት ሬፓብሊክ ኮንጎ ሰሜናዊ ክልል በምትገኘው በዶንጎ ከተማ ተከስቶ በነበረው ግጭት ሳቢያ 100 ሰዎች ለሞት አደጋ እና 25 ሺሕ የሚገመቱት ለመፈናቀል አደጋ መጋለጣቸው የተባበሩት መንግሥታት RealAudioMP3 ያሰራጨው መግለጫ የጠቀሰው ሚስና የዜና አገልግሎት አስታውቀዋል።

የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ ጉዳይ የሚመለከተው ጽ/ቤት ቃል አቀባይ ማውሪዚዮ ጁሊያኖ ግጭቱ ከተገታ ይኸው አንደኛ ሳምንቱ ያገባደደ ቢሆንም በዚህች ከተማ ዋና ዋና መንገዶች አሁንም የአንዳንድ የተገደሉት ሰዎች አስከሬን ገና አለ መነሳቱ ገልጠው፣ የተፈናቀለው ሕዝብ ለተለያዩ ሰብአዊ ችግሮች ተጋልጦ እንደሚገኝ፣ ሱቆች መኖሪያ ቤቶች በእሳት መጋየታቸውንም አብራርተው፣ የዚህ ግጭት ሰለባ የሆኑት እና በተለይ ደግሞ ሕጻናት አስቸኳይ የሰብአዊድጋፍ እንደሚያሻቸው እና በዚሁ ረገድ የተባበሩት መንግሥታት አስቸኳይ የምግብ እና የመድሃኒት እርዳታ እያቀረበ መሆኑ ገልጠው፣’ ሁሉም የግብረ ሰናይ ማኅበራት የተቻላቸውን እንዲያደርጉ ጥሪ ማቅረባቸው ሚስና የዜና አገልግሎት አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.