2009-11-23 15:23:28

የካቶሊክ እና የአንግሊካን ኣቢያተ ክርስትያን ጥብቅ ግኑኝነት


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ከትላትና በስትያን የአንግሊካን ቤተ ክርስትያን የበላይ መንፈሳዊ መሪ የካንተርበይ ሊቀ ጳጳሳት ሮዋን ዊሊያምስን ተቀብለው ማነጋገራቸው የቅድስት መንበር RealAudioMP3 መግለጫ አረጋገጠ።

በዚህ የሁለቱ አቢያተ ክርስትያን ግኑኝነት ወቅት በዚህ ባለንበት ዘመን የክርስትያን ማኅበርሰብ እያገጠመው ያለው እክል በመወያየት የሁለቱ አቢያተ ክርስትያን ግኑኝነት መጠበቅ አጠናክሮ ለማነቃቃት እና እንዲሁም ይኽንን ጥብቅ ግኑኝነት ለመመስከር ምን መደረግ እንዳለበት መወያየታቸውም መግለጫው ያመለክታል። የጋራ ምስክርነት የሁለቱ አቢያተ ክርስትያናት ለውህደት የሚያደርጉት ጥረት ያለው ሙሉ ፍላጎት በጸና ትብብር በመከናወን ላይ መሆኑ የሚያረጋገጥ እና በዚህ መንፈስ መቀጠል እንዳለበትም መክረዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የሁለቱ አቢያተ ክርስትያን የጋራው ድርገት የአንግሊካን እና የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ለሚያከናውኑት ሶስተኛው ዓለም አቀፍ የቲሊዮጊያ ውይይት መርሃ ግብር ለማሰናዳት እንደሚገናኙ የቅድስት መንበር መግለጫ ያረጋገጣል።








All the contents on this site are copyrighted ©.