2009-11-23 15:27:53

የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ውሳኔ የጸደቀበት 30ኛው ዝክረ ዓመት


የዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ውሳኔ የዛሬ 30 ዓመት በፊት በትክክል እ.ኤ.አ. በ 1979 ዓ.ም. ከታወጀበት ወዲህ የሴቶች ሁኔታ በዓለማችን ምን እንደሚመስል የሚወያይ ዓለም አቀፍ ጉባኤ በሮማ እፊታችን RealAudioMP3 ህዳር 25 ቀን 2009 ዓ.ም. እንደሚካሄድ ተገለጠ።

ይህ ውሳኔ የዘር የጾታ እና የጎሳ የቀለም አድልዎ ፍፈጽሞ እንዲሻር የሰው ልጅ በመብት እና በፈቃድ እኵል መሆኑ የሚያረጋግጥ መሆኑ ሲታወቅ፣ የሴቶች መብት እና ፈቃድ መከበር አሁንም ምሉ በሙሉ ተረጋገጦአል ለማለት እንደማይቻል ባንዳንድ አገሮች በሴቶች ላይ የሚፈጸመው በደል የሚመሰክረው ሲሆን፣ በብራዚል ሴቶች ለአመጽ በአፍጋኒስታን ሴቶች የበታች ሆነው ለዘርፈ ብዙ ችግሮች ተጋልጠው እና በዚህች አገር በ27 ደቂቃ ውስጥ አንዲት ሴት በምጥ እንደምትሞት፣ በተለያዩ አገሮች ሠራተኛ ሴቶች ከባልደረቦቻቸው ወንዶች ዝቅ ያለ ደሞዝ እንደሚከፈላቸው፣ በተለያዩ በበለጸጉት አገሮች ሴቶች በባሎቻቸው እጅ ለሞት እንደሚዳረጉ ስለ ሴቶች ጉዳይ የሚንከባከበው የፓንጄአ የግብረ ሠናይ ማኅበር ሊቀ መንበር ሲሞና ላንዞኒ ከቫቲና ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ በመግለጥ፣ በርግጥ በነዚህ ባለፉት 30 ዓመታት ስለ ሴቶች ብዙ ተደርገዋል፣ ሆኖም ግን ውጤቱ ገና እንደተጠበቀው አይደለም ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.