2009-11-23 15:26:22

ታይዋን ወንጌል የተቀበለችበት 150ኛው ዓመት


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ታይዋን ወንጌል የተቀበለችበት 150ኛው ዓመት ምክንያት በማድረግ በሚካሄደው መንፈሳዊ ባህላዊ በዓል እሳቸውን ወክለው በመሳተፍ ላይ ለሚገኙት የአስፍሆተ ወንጌል የሚንከባከበው ቅዱስ RealAudioMP3 ማኅበር ኅየንተ ለነበሩት ብፁዕ ካርዲናል ጆሰፍ ቶምኮ መልእክት ማስተላለፋቸው የሚዘከር ሲሆን። ታይዋን ወንጌል የተቀበለችበት 150ኛው ዓመት ምክንያት ሲካሄዱ የሰነበቱት መንፈሳዊ እና ባህላዊ መርሃ ግብሮች ትላትና እሁድ ህዳር 22 ቀን 2009 ዓ.ም. ብፁዕ ካርዲናል ጆሰፍ ቶምኮ በመሩት መሥዋዕተ ቅድሴ ተፈጽሟል።

የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የክርስቶስ ንጉሥ ዓመታዊ በዓል ባከበረችበት ዕለት የተፈጸመው 150ኛ ዓመት ታይዋን ወንጌል የተቀበለችበት ዓመት ለተደረገው በዓል ለየት እንዳደረገው ቅዳሴውን የመሩት ብፁዕ ካርዲናል ቶምኮ ባሰሙት ስብከት በመግለጥ፣ ይኽ በዓል በታይዋን አስፍሆተ ወንጌል ዳግም ታድሶ ይከናወን ዘንድ የሚያነቃቃ ኃላፊነት እንዳለ የሚያመለክት ነው እንዳሉ ተረጋገጠዋል። የእግዚአብሔር መንግሥት ወታደራዊ ኃይልም ሆነ ኤኮኖሚያዊ ሃብት የለውም፣ መንግሥቱ በፍቅር የሚገለጥ ፍቅርን የሚመሰክር ፍቅር የሚኖርበት ነው፣ ካሉ በኋላ የታይዋይን ቤተ ክርስትያን ከኵላዊት ቤተ ክርስትያን ጋር ያለውን ትስስር ፈጽማ ሳታጎድል ብፁዓን አቡናት ካህናት ገዳማውያን ለቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ያላቸው ታዛዥነት በመጠበቅ ኅብረታቸውን ይመሰክሩ ዘንድ አደራ ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.