2009-11-18 13:50:44

የቤተ ክርስትያን ሓዋርያዊ ግብረ ተልእኮ አገልግሎት


የአህዛብ ስብከተ ወንጌል የሚንከባከበው ቅዱስ ማኅበር ያነቃቃው፣ ወንጌል በትክክል ለማስፋፋት እና የእግዚአብሄር ፍቅር በማኅብረሰብ ልብ እንዲሰርጽ ለማድረግ እና ይህ የአስፍሆተ ወንጌል ተቀዳሚ ዓላማ ግቡን እንዲመታ ምን ዓይነት መንገድ RealAudioMP3 መከተል ይኖርበታል ለሚለው ጥያቄ መልስ ለመጠት ያነሳሳው ስለ ጉዳይ የሚወያይ ይፋዊ መደበኛው ስብሰባ ከትላትና በስትያ ጀምሮ እዚህ ሮማ በሚገኘው በጳጳሳዊ ኡርባኒያኑም መንበረ ጥበብ በመካሄድ ላይ ሲሆን፣ የስብሰባው ዋናው ርእስ ቅዱስ ጳውሎስ እና ወቅታዊው አስፍሆተ ወንጌል የሚል መሆኑ ተገልጠዋል፣

ይህ ቅዱስ ማኅበር በአፍሪቃ በእስያ በኦቸያኒያ በካናዳ በተባበሩት የአሜሪካ መንግሥታት በላቲን አሜሪካ ብቻ ሳይሆን ክርስትና ገና አንድ ብሎ ሲጀምር ወንጌልን እና ክርስትናን በተቀበለቱ በጥናታውያን የክርስትና አገሮች ጭምር የሚከናወነው አስፍሆተ ወንጌል የሚንከባከብ ሲሆን፣ ይህ በመካሄድ ላይ ያለው ስብሰባ በዚህ በምንኖርበት በሰለጠነው ዘመን የሚሰጠው ወንጌላዊ አገልግሎት እና የአስፍሆተ ወንጌል ተልእኮ በሚገባ ግቡን እንዲመታ መከተል የሚገባው ስልት ለመለየት መሆኑ የጊኒ ቢሳው ርእሰ ከተማ ኮናክሪ ሊቅ ጳጳስ የነበሩት የዚህ ቅዱስ ማኅበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ኣቡነ ሮበርት ሳራህ ከቫቲካን ሬዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ አብራርተው፣ የወንጌላዊ አገልግሎት እና የአስፍሆተ ወንጌል አብነት ቅዱስ ጳውሎስ ነው ስለዚህ እያንዳንዱ ወንጌላዊ ልኡክ እንደ ቅዱስ ጳውሎስ የክርስቶስ ቅርብ ጓደኛ በክርስቶስ ፍቅር የተሞላ እና ፍቅሩን ለሌሎች ለማስድረስ የሚችል መሆን አለበት፣ በዚህ ፍቅር ያልተሞላ ወንጌልን ለሌሎች ለማቅረብ ፈጽሞ አይቻለውም፣ ካሉ በኋላ ክርስቶስ የተቀበለ ዓለማዊ ምእመን ጭምር የዚህ ተልእኮ ተሳታፊ መሆን አለበት ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.