2009-11-18 13:52:36

የሕጻናት ወተደሮች ጉዳይ


የጨቅላነት ሕይወት የተነፈጋቸው ለውትድርና ዓለም የተዳረጉት ሕጻናት ጉዳይ የሚወያይ ዓለም አቀፍ ስብሰባ በኢጣሊያ ቶሪኖ ከተማ በሚገኘው የወታደራዊ ትምህርት ተግባር እና የስነ መከላከያ ኃይል ተቋም RealAudioMP3 የጉባኤ አዳራሽ ከትላትና በስትያ መከናወኑ ተገለጠ።

ሕጻናትን በውትድርናው ዓለም የመዳረጉ አሰቃቂው ተግባር በአለማችን በጠቅላላ 300 ሺሕ ሕጽናት የሚመለከት ሲሆን፣ የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ይኸንን የሕጻናት ሰብአዊ መብት እና ፈቃድ የሚጥስ አሰቃቂ ተግባር ጨርሶ ለማስወገድ የተሳነው እንደሚመስል በጉባኤው የተሳተፉት ንግግር ያሰሙት የዓለም አቀፍ ፖለቲካ ጥናት ተቋም የስብአዊ መብት እና ፈቃድ የሚከታተለ ዘርፍ አቀነባባሪ ፕሮፈሶር ጆርጆ ግረፒ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ምንም’ካ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሕጻናት መብት እና ፈቃድ በሚመለከቱ ጉዳዮች የተለያዩ ውሳኔዎች የተላለፉ ቢሆንም ቅሉ፣ ችግሩ ጨርሶ አልተወገደም እንዳውም እየተስፋፋ በመሄድ ላይ ነው ብለዋል።

በዓለማችን በተለያዩ ጦርነት እና ውጥረት በሚታይባቸው 80 አገሮች በጠቅላላ 300 ሺሕ ሕጻናት ያካተተ መሆኑ ፕሮፈሶር ግረፒ በመግለጥ፣ የወታደር ሰብአዊ መብት እና ፈቃድ በዓለም አቀፍ ግጭቶች ብቻ ሳይሆን፣ የርስ በርስ ግጭት እንዲሁም በጎረቤት አገሮች ውጥረት ባለበት ወቅት ጭምር መከበር ይኖርበታል፣ በማለት በማንኛው ዓይነት ግጭት ሕጻናትን ለውትድርናው ዓለም ማስገደድ ጨርሶ ጸረ ሰብአዊ ተግባር መሆኑ ሁሉም አገሮች የሚያውቁት ጉዳይ ነው፣ በቀጥታ መግንሥታት የሚጥሱት ውሳኔ ሳይሆን፣ ሽምቅ ተዋጊዎች፣ የተለያዩ የነጻነት ግንባር ነን ባዮች፣ የወንጀል ቡድኖች የሚፈጽሙት ጸረ ስበአዊ ተባር ነው፣ ስለዚህ ሕጻናትን ለዚህ ዓይነቱ አደጋ የሚያጋልጡ በጸረ ሰብአዊ ወንጀል መጠየቅ ይኖርባቸው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.