2009-11-18 13:58:08

እያንዳንዱ አማኝ የሚከበርባት ኤውርጳ


የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ የነበሩት የካርዲናሎች አፈ ጉባኤ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ሶዳኖ ላንዲት አዲሲቷ ኤውሮጳ የክርስትያኖች አስተዋጽኦ በሚል ርእስ ሥር የደረሱት መጽሓፍ ሮማ በሚገኘው የኤውሮጳ መንበረ ጥበብ ተገኝተው በሰጡት መገለጫ RealAudioMP3 ለንባብ መቅረቡ ተገለጠ። ብፁዕ ካርዲናል ሶዳና ባሰሙት ንግግር ማንም ሃይማኖታዊ መንግሥት ለማጽናት የሚያልም ሆነ የሚፈልግ የለም ነገር ግን ማንኛውም ሃይማኖት በትምህርት ቤትም ሆነ በባህል መድርክ እና በግብረ ሰናይ አገልግሎት እምነቱን ይገልጥ ዘንድ አስፈላጊ ነው፣ ስለዚህ ኤውሮጳ ይህ መንፈስ የሚንጸባረቅባት ክፍለ ዓለም መሆን ይገባታል ብለዋል።

ኤውሮጳ ሃይማኖታዊ እና መንፈሳዊ መሠረት ያላት ሆና ይህ ክብር የሚረገጥባት መሠረታዊ እሴቶቿ የሚካድባት ልቅ ዓለምዊንት የሚኖርባት መሆን የለባትን ካሉ በኋላ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የፕሮተስታንት አቢያተ ክርስትያን እና የኦርቶዶክስ አቢያተ ክርስያን ኤውርጳ የባህል መሠረቷ እንዳይካድ በሚድረገው ጥረት አቢይ አስተዋጽኦ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.