2009-11-17 09:49:39

የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ትኩረት የሰጠ ጉባኤ እና የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ንግግር፡



 


የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ትኩረት የሰጠ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ዛሬ እዚህ ሮማ ውስጥ ተጀምረዋል።

የፋኦ የምግብ እና ተቋም ዋና ጸሐፊ አብዶ ዲዮፍ ከሚራቡ ህዝቦች ጋር ለመተባበር በጉባኤው ዋዜማ ለትናንትና ሰንበት በዓለም አቀፍ ደረጃ የአንድ ቀን የምግብ ላለመውሰድ አድማ እንዲካሄድ አሳስበው ነበር ።

የምግብ ዋጋ እየናረ በመሄዱ የደቡባዊ ምስራቅ ኤስያ እና በትህተ ሰሀራ የሚገኙ ህዝቦች ለኀለኛ ርሀብ መጋለጣቸው የተባበሩት መንግስታት የእርሻና መግብ ተቋም አስታውቀዋል ።

በግጭቶች እና ባለመረጋጋት የሚሰቃዩ ሀገራት በምግብ እጦት በአስከፊ ሁኔታ እንደሚገኙ ያመለክተው የምግብ ተቋሙ የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ የዓለም መንግስታት ሁነኛ ርምጃ እንዲወስዱ አጽንኦት ሰጥቶ እያሳሰበ ነው ።

በዚሁ ዛሬ የተጀመረው የምግብ ዋስትና ትኩረት የሰጠ አገሮች አቀፍ ጉባኤ የስልሳ ሀገራት መንግስታት እና የአገሮች አቀፍ ድርጅቶች ተውካዮች ተሳታፊ መሆናቸው ተገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት አንድ ሚልያርድ አንድ መቶ ሚልዮን የዓለም ህዝብ የርሐብ ሰለባ መሆኑ የእርሻና ምግብ ተቋሙ ጠቅሶ የዓለም ህዝቦች ከርሐብ በኢንዱስትሪ የበለጠጉ ሀገራት የታዳጊ ሀገራት የምግብ እጦት ለማርገብ በእርሻ መዋእለ ንዋይ እንዲያፈሱ እና ኢንቨስት እንዲያደርጉ እየተጠየቁ መሆናቸው ተመልክተዋል።

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቅቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በዚሁ ዛሬ እዚህ ሮማ ውስጥ በሚገኘው የእርሻና መግብ ተቋም ዋና ፅሕፈት ቤት የተከፈተው ዓለም አቅፍ ጉባኤ መክፈቻ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል ።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በዚሁ ዓለም አቀፍ የምግብ ውስትና ትኩረት የሰጠ የመሪዎች ጉባኤ ተገኝተው ፡ የፋኦ የእርሻና ምግብ ተቋሙ ዋና ጸሐፊ አብዱ ዲዩፍ ያደረጉላቸው ጥሪ በማመስገን ባሰሙት ንግግር ፡ ዓለም አቀፉ ኅብረተሰቡ በዚሁ ዓመታት ከባድ የኤኮኖሚ እና የፋይናንስ ቀውስ እንደገጠም አስታውሰው ፡ ስትቲስትክስ እንደሚያሳየው በምግብ እጦት የሚሰቃይ ህዝብ ቁጥር ከፍ ማለቱ እንደሚያስረዳ ጠቁመው ቤሌላ በኩል ደግሞ ዓለማችን የሚኖርባት ህዝብ ለመመገብ ችሎታ እንዳላት እንደሚመለከት ገልጸዋል።

የዓለም መንግስታት ለምግብ እጦት ጠንቅ የሆኑ ሀገራት በማስውገድ በታዳጊ ሃገራት እርሻ የልማት ኢንቨስትመንት እንዲያደርጉ አሳስበዋል ።

በአሁኑ ወቅት በዓች አለም ላይ ያነስው የገንዘብ ማመንጫ ሀብት እጥረት ሳይሆን ማሕበራዊ ኢ ፍትሀውነት እና ለሁሉም የማይደርስ ያልተስካካለ ሀብት ስላለ መሆን ኡ ቅዱስ አባታን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ዛሬ ረፋድ ላይ በየእርሻ እና ምግብ ተቋም የተጅመረው ሀገራት አቀፍ የምሪዎች ጉባኤ ተገኝተው ገልጸዋል ።

የበለጸጉ ሀገራት ለታዳጊ ሀገራት መሰረተ ልማት እድገት ትኩረት እንዲሰጡም የካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ለጉባኤኞች ተማጽነዋል።

በሚልዮን የሚቅጠሩ ህዝቦች ሕይወት እየቀዘፈ ያልው ርሐብ ለመግታት እና ብሎም ለማውደም የዓለም መንግስታት እና ባለ በጎ ፈቃድ ስዎች ሐልፊነት መሆኑንም ቅድስነታቸው አያይዘው ገልጸዋል ።

ሙሉ ሰብአዊ እድገት ርሐብን ለመታገል እንደሚያገለገል ያመለከቱት ርእሰ ሊቃነ ፡ጳጳሳት በነዲክቶስ የመንግስታት ትብብር እንደሚያስፈልግ እና ከሁሉም በላይ ደግሞ የሰው ልጅ የመመገብ መሰረታዊ መብት መጠበቅ እንዲሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።

በጨካኝ እና ቀሳፊ በሆነ ርሐብ ህዝቦች እየተቀዘፉ ምግብ ነክ ጉዳዮች ሲብባክኑ ማየት አሰቃቂ ድርጊት መሆኑ ጠቅሰው ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ርሐብን ለመግታት በሚደረጉ ትግሎች አብራ እንደምትሰራ አውረጋግጠው ላዳመጥዋቸው የስብሰባው መሪዎች አመስገነው ሓዋርያዊ ቡራኬ ሰጠው እና ተሰናብተው በሰላም ወደ ሓዋርያዊ መንበራቸው ተመልሰዋል ።








All the contents on this site are copyrighted ©.