2009-11-16 14:00:40

ኬንያ፣ የሕገ መንግሥት ተሃድሶ


በኬንያ ሕገ መንግሥት ለማሻሻል የተወጠነው ዕቅድ እና የተጀመረው ሂደት የኬንያ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን እንደምትደገፈው አስታውቃለች። እ.ኤ.አ. ከኅዳር 10 እስከ ሕዳር 11 ቀን 2009 ዓ.ም. የኬንያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት RealAudioMP3 የአገሪቱ ሕገ መንግሥት ርእስ በማድረግ ዓውደ ጥናት ማካሄዱ እና እንዲሁም የኬንያ ብሔራዊ የአቢያተ ክርስትያን ምክር ቤት ጭምር ተመሳሳይ ስብሰባ በማካሄድ ሕገ መንግሥት የአገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ እግምት ውስጥ በማስገባት ኃላፊነት ግልጽነት የሚያጎላ የሕዝብ ተሳትፎ የሚያነቃቃ መሆን እንዳለበት ማሳሰቡ ሎሶርቫቶረ ሮማኖ የተሰኘው የቅድስት መንበር ዕለታዊ ጋዜጣ ይጠቁማል። ይህ በንዲህ እንዳለመ በሕገ መንግሥት ሊቃውንት እና የፖለቲካ አካላት አማካኝነት የሚቀርበው የህገ መንግሥት የማሻሻያው ሰነድ እና የታደሰው ሕገ መንግሥት ንድፍ ጭምር ለሕዝባዊ ድምጸ ውሳኔ መቅረብ እንደሚገባው የኬንያ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን እና ይህ የኬንያ ብሔራዊ የአቢያተ ክርስትያን ምክር ቤት በማሳሰብ፣ የዜጎች እኩልነት የሚያረጋግጥ የሁሉም ሰብአዊ መብት እና ፈቃድ እንዲሁም ግዴታንም ጭምር የሚያነቃቃ የአገሪቱ ሕዝብ መሠረታውያን ፍላጎቶች ይረጋገጥለትም ዘንድ ዋስትና የሚሰጥ መሆን እንዳለበት አሳስበዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.