2009-11-16 13:59:29

ኤውሮጳ ቻይና እና አፍሪቃ ለአዲስ የዓለም አቀፍ እድገት ጎዳና


የቅዱስ ኤጂዲዮ ማኅበር ያነቃቃው በሮማ ሲካሄድ የሰነበተው ኤውሮጳ ቻይና እና አፍሪቃ ለአዲስ የዓለም አቀፍ እድገት ጎዳና በሚል ርእሰ ጉዳይ የተወያየው ዓለም አቀፋዊ ስብሰባ በተጠናቀቀበት እለት በተሰጠው ጋዜጣዊ መገልጫ የተሳተፉት RealAudioMP3 በጉባኤው የተገኝተው ንግግር ያሰሙት የኢጣሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒ. ለአፍሪቃ ጉዳይ ተጠሪ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚን. ጁዜፐ ሞራቢቶ ለአፍሪቃ እድገት አፍሪቃ በእርዳታ ብቻ መደገፍ፣ ከሚለው ከረጂ እና ተረጂ ግኑኝነት መላቀቅ እና ስለ አፍሪቃ የሚሰጠው ቅድመ ፍርድ ማስወገድ እጅግ አስፈላጊ ነው ብለዋል።

በዚህ የፖለቲካ አካላት የኤኮኖሚ እና የባህል ሊቃውንት ጭምር ያሳተፈው ዓለም አቀፍ ስብሰባ ኤውሮጳ አፍሪቃ እና ቻይና፣ አፍሪቃ በዚህ ዓለማዊ ትሥሥር በጎላበት ዓለም ተገቢ ሥፍራ በማግኘት በዓለም አቀፍ መድረኮች ድምጽዋን ለማሰማት ትችል ዘንድ የተካሄደው ስብሰባ በማሳሰብ፣ በዓለማችን የሚታየው ኤኮኖሚያዊ ውደራ በማደግ ላይ ለሚገኙት አገሮች ዕድል የማይሰጥ መሆኑ የተካሄደው በመግለጥ፣ በዚህች ክፍለ ዓለም ኤኮኖሚያዊ ማህበራዊ ፖለቲካዊ መረጋጋት ማረጋገጥ ለአፍሪቃ እድገት እጅግ ወሳኝ መሆኑ የቅዱስ ኤጂዲዮ ማኅበር ሊቀ መንበር ማርኮ ኢምፓሊያዞ በማሳወቅ፣ የምዕራቡ ዴሞክራሲ አፍሪቃ የችግር የድኽነት የውጥረት የስደት ክፍለ ዓለም በማድረግ ሲመለከታት እና በዚህ አኳያ ከአፍሪቃ አገሮች ጋር የሚያካሂዱት ግኑኝነት መሠረት ያደረገ ሲሆን፣ ቻይና አፍሪቃ እድል እድርጋ እደምትመለከታት በጉባኤው የተሳተፉት እና ንግግር ያሰሙት በፐኪን የስነ ማኅበራዊ ሳይንስ መምህር እሄ ወንፒንግ አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.