2009-11-16 14:02:24

አፍሪቃ እንዳትረሳ


ባለፉት ቀናት ከፈረንሳይ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ጋር የተገናኙት በቻድ የሳርህ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤድሞንድ ድጂታንጋር ቤተ ክርስትያን የእግዚአብሔር ቤተሰብ ከሚለው መሠረታዊ ቲዮሎጊያዊ ፍቹ በማስቀደም፣ RealAudioMP3 የኤውሮጳ ቤተ ክርስትያን አፍሪቃን እንድታስታውስ እና በበለጸጉት አገሮች እንዳትረሳ ለኤውሮጳ ቤተ ክርስትያን ጥሪ ማቅረባቸው ተገልጠዋል።

በተካሄደው ግኑኝነት ብፁዕ አቡነ ድጅታንጋር በቅርቡ እዚህ በቫቲካን የተካሄደው ሁለተኛው የአፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ርእስ በማድረግ ንግግር በማሰማትም በአፍሪቃ የሚታዩት ጎሳዊ ግጭቶች፣ ያደንዛዥ እጽዋት መስፋፋት፣ የስደተኞች ሁኔታ፣ የጦር መሣሪያ ንግድ ሙስና የመሳሰሉት አበይት ችግር ማስወገድ ተቀዳሚ ዓላማ መሆን እንደሚገባው ሁለተኛው ሲኖዶስ ማሳሰቡንም አስታውሰው፣ የአፍሪቃ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን በአፍሪቃ የሚታዩት ፖሊቲካዊ ማኅበራዊ እና ሰብአዊ ችግሮች በዝምታ ማየት እንደማይገባት ጠቅሰው የአፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት በዚህ ረገድ ተቀዳሚው ሚና መጫወት እንዳለባቸውም አበክረዋል።

የሕይወት ክብር መጠበቅ እሴቶች ለትውልድ ማስተላለፍ፣ ሰብአዊ ግብረ ገባዊ እና ስነ ምግባራዊ ሕንጸት በአፍሪቃ በማስፋፋት ወደ ግጭት ብሎም ለስደተ የሚዳርጉት በአፍሪቃ የሚቀሰቀሱት እክሎች ቀድሞ መፍትሔ እንዲያገኙ ማድረግ ለአፍሪቃ ሰላም ወሳኝ ነው እንዳሉም ለማወቅ ተችለዋል። የአናሳ ሃይማኖቶች እና ጎሳዎች መብት እና ፈቃድ ጥበቃ በማኅበራዊ እና በቤተክርስትያን የሴቶች ተሳትፎ ማነቃቃት እና ማጎልበት አስፈላጊ ነው እንዳሉም ከፈረንሳይ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የተሰራጨው ዜና ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.