2009-11-16 13:56:45

ታይዋን ወንጌል የተቀበለችበት 150ኛው ዓመት


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ታይዋን ወንጌል የተቀበለችበት 150ኛው ዓመት ምክንያት በማድረግ በሚካሄደው መንፈሳዊ ባህላዊ በዓል እሳቸውን ወክለው በመሳተፍ ላይ ለሚገኙት የአስፍሆተ ወንጌል የሚንከባከበው ቅዱስ ማኅበር RealAudioMP3 ኅየንተ የነበሩት ብፁዕ ካርዲናል ጆሰፍ ቶምኮ መልእክት ማስተላለፋቸው ተገለጠ።

ታይዋን ወንጌል የተቀበለችበት 150ኛው ዓመት ምክንያት እየተካሄዱ ያሉት መንፈሳዊ እና ባህላዊ መርሃ ግብሮች እ.ኤ.አ. ህዳር 22 ቀን 2009 ዓ.ም. በሚፈጸመው ዓቢይ በዓል እንደሚጠናቀቅ ቅዱስ አባታችን ባስተላለፉት መልእክት በማስታወስ፣ ወንጌል ለታይዋን አቢይ መንፈሳዊ ሃብት ማጎናጸፉ እና የአገሪቱ ህዝብ በወንጌል አማካኝነት ከእግዚአብሔር መልካም የሆነውን ሁሉ ለመቀበል መቻሉ እና በእግዚአብሔር መደገፉንም ጠቅሰው፣ ይህ በዓል ማክበር ተገቢ ነው ብለዋል። ቅዱስ አባታችን በብፁዕ ካርዲናል ቶምኮ በኩል ባስተላለፉት መልእክት ይህ አቢያ በዓል የላቲን ሥርዓት የምትከተለው የታይዋይ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን በክርስቶስ የዓለም ንጉሥ በዓል በሚከበርለት ዕለት በመሆኑም መንፈሳዊነቱ እጅግ ድርብ እና ጥልቅ ነው ብለው፣ ቅድስት መንበር ለታይዋን ህዝብ እና ምእመናን እንዲሁም ለውሉደ ክህነት እና ገዳማውያን ቅርብ መሆኑዋ ቅዱስ አባታችን ባስተላለፉት መልእክት በመግለጥ፣ ይህ ቅርበት ብፁዕ አቡነ ቶምኮ ይመሰክሩ ዘንድ እና ሓዋርያዊ ቡራኬአቸውንም ያቀርቡ ዘንድ አደራ ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.