2009-11-16 13:55:25

ሰርቢያ የኤውሮጳ ኅብረት አገሮች አባል ለመሆን


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ባለፈው ቅዳሜ የሰርቢያ ርእሰ ብሔር ቦሪስ ታዲችን ተቀብለው በማነጋገር፣ በተካሄደው ግኑኝነት የባልካን ክልል አገሮች ወቅታዊው ሁኔታ እና ሰርቢያ የኤውሮጳ ኅብረት አባል RealAudioMP3 ለመሆን እያከናወነቸው ያለው ጉዞ ርእስ በማድረግ መወያየታቸው የቅድስት መንበር መገልጫ ያመለክታል።

በግኑኝነት ወቅት ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን በሰርቢያ የምትሰጠው መንፈሳዊ ሰብአዊ እና ማኅበራዊ አስተዋጽኦ በአገሪቱ መንግሥትም ሆነ በህዝብ የላቀ እውቅና ያለው መሆኑ የተሰመረበት ሲሆን፣ በካቶሊክ እና በሰርቢያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን መካከል ያለው የጋራው ግኑኝነት አወንታዊ መሆኑ ተጠቅሰዋል።

የሰርቢያው ርእሰ ብሔር ታዲች ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ ግኑኝነት በመቀጠል በቅድስት መንበር የውጭ ግኑኝነት ጉዳይ ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ዶሚኒክ ማምበርት የተሸኙት ከቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶነ ጋር መገናኘታቸው የቅድስት መንበር የዜና እና የምኅተም ክፍል ያሰራጨው መገልጫ ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.