2009-11-13 13:33:25

ኮንጎ


በኮንጎ ሰሜናዊ የኤኳቶር ክልል መሣሪያ በታጠቁት የኤንይለ ጎሳ እና በአገሪቱ የጸጥታ ሃይሎች መካከል በተከሰተው ግጭት ሳቢያ 10 ሺሕ ሕዝብ ቤቱን እና ንብረቱን በመተው መፈናቅሉ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች እና RealAudioMP3 የተፈናቃዮች የበላይ ድርጅት አስታወቀ።

በዚህ አሁንም 24 ሺሕ 194 የክልሉ ነዋሪው ሕዝብ ለመፈናቀል አደጋ መጋለጡ የበላይ ድረገት በመግለጥ፣ ለተፈናቀለው ህዝብ እርዳታ ለማቅረብ ተከስቶ ያለው ግጭት መግታት ወሳኝ ሲሆን፣ የተፈናቀለው ህዝብ በኡባንግይ እና እንዲሁም በኤበኮ ወንዝ ዳርጃ መስፈሩ ድርጅቱ በማሳወቅ፣ በክልሉ የተሰማራው የጸጥታው ኃይል አንዳንድ ግጭቱን ያነሳሱት እና የክልሉን ህዝብ ለሞት የዳረጉት 100 የሚሆኑ ሰዎችን በቁጥጥር ሥር በማዋላሉ ምክንያት በክልሉ ያለው ሁከት ገታ እያለ መምጣቱ የአገሪቱ የዜና አውታሮች ይጠቁማሉ።

ይህ በእንዲህ እንዳለም ተከስቶ ያለው ግጭት ለመግታት እና ያስከተለው የሰው እና የንብረት ጉዳት ለመገምገም በኮንጎ ለደጥታ እና ለደህንነት የተሰማራው የተባበሩት መንግሥታት የልኡካን ቡድን ተጠሪ እና የአገሪቱ የውስጥ ጉዳይ ሚኒ. ተወካዮች የሚገኙባቸው ልኡካን ውጥረት ወደ አለበት ክልል መላኩ ተገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.