2009-11-13 13:31:05

አፍሪቃ፣ የምግብ እጥረት


የተባበሩት መንግሥታት የምግብ እና የእርሻ ድርጅት ካሰራጨው መገልጫ ለመረዳት እንደተቻለው፣ በአፍሪቃ 31 አገሮች በጠቅላላ 20 ሚሊዮን የሚገመት ሕዝብ የምግብ እርዳታ ያስፈልገዋል፣ በአፍሪቃ በተለይ ደግሞ RealAudioMP3 ምስራቅ አፍሪቃ እራስን በምግብ አቅርቦት የመቻሉ አቅም እጅግ ወደ ኋላ እየተጎተተ፣ በብዙ ሚሊዮን የሚገመተው ሕዝብ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልገው እና ድርቅ ከሚያስከትለው ችግር ሌላ በዓለማችን የተከሰተው የኤኮኖሚ መቃወስ ምክንያት እየተስፋፋ ያለው የኑሮ ወድነት በዚሁ ክልል ከቀን ወደ ቀን ከሕዝብ የኤኮኖሚ አቅም እጅግ እየራቀ ለተጨማሪ የርሃብ እና የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ተጋልጦ እንደሚገኝ የፋኦ መገልጫ ይጠቁማል።

የተባበሩት መንግሥታት የሕናነት ጉዳይ የሚንከባከበው ማኅበር፣ ለአፍሪቃ ቅርንጫ ዋና አስተዳዳሪ ፐር ኤንገባክ በተመጣጠነ ምግብ እጥረት የሚጠቁት የአፍሪቃ ሕጻናት ጉዳይ እጅግ አሳሳቢ መሆኑ በመግለጥ፣ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት አንገብጋቢ ነው፣ ስለዚህ የዓለም አቅፍ ማኅበሰብ በተመጣጠነ ምግብ እጥረት ሳቢያ ለተለያዩ የጤና መጓደል አደጋ እየተጠቁ ላሉትን ለምስራቅ አፍሪቃ ሕጻናት እርዳታ ያቀርቡ ዘንድ ጥሪ አቅርበዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.