2009-11-13 13:28:03

አደገኛው ጸረ ሴማዊነት ተግባር


የክርስትያኖች አንድነት የሚንከባከበው ጳጳሳዊ ምክር ቤት እና ከአይሁድ ሃይማኖት ጋር የሚደርገውን ግኑኝነት የሚንከባከበው ድርገት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ቫልተር ካስፐር የበይሎሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ፓትሪያርክ RealAudioMP3 ብፁዕ ወቅዱስ ፊላረት ባደረጉላቸው ጥሪ መሠረት በሚንስክ ሓዋርያዊ ጉብኝት በማካሄድ እና እዛው በአይሁድ እና በክርስትያን እምነት መካከል ያለውን ግኑኝነት፣ ሃይማኖታዊ እሴቶች ለጋራ መከባበር መሠረት፣ በሚል ርእስ ሥር በተካሄደው ዓውደ ጥናት ተሳትፈው፣ ትላትና ወደ ቫቲካን ተመልሰዋል።

ብፁዕነታቸው ቫቲካን እንደደረሱ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ይህ በሳቸው የሚመራው ጳጳሳዊ ምክር ቤት በበይሎሪሲያ የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ጋር መልካም እና የተዋጣለት ግኑኝነት እንዳለው ገልጠው፣ በተለይ ደግሞ ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ ፊላረተ ጋር ያለው ግኑኝነት የሚደነቅ ነው ብለዋል። በሚኒስክ ሁለቴ ሓዋርያዊ ጉብኝት ማካሄዳቸው እና በዚሁ በሁለተኛው ሓዋርያዊ ጉብኝታቸው በአይሁድ እና በክርስትናው እምነት መካከል ስላለው ግኑኝነት በተወያየው ዓወደ ጥናት መሳተፋቸውም ጠቅሰው፣ በአይሁድ እና በክርስትናው እምነት መካከል የሚደረገው ውይይት በጣም ጥንቃቄ እንደሚያሻውም በማስታወስ፣ በምስራቅ ኤውሮጳ በተለይ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በፊት ብዙ አይሁዳውያን ይኖሩ እንደነበር፣ ሆኖም ግን በወቅቱ ተከስቶ በነበረው ጸረ ሴማዊ ርእዮት ምክንያት ብዙዎች ታድነው እና ላሰቃቂው እልቂት ተጋልጠው ብዙዎቹ ለስደት በመገደዳቸው ምክንያት በዚሁ ክልል ያሉት ያይሁድ እምነት ተከታዮች በጣም አናሳ የኅብረተሰቡ ክፍል ሆነው ቀርተዋል። በአይሁድ እምነት ተከታዮች የደረሰው አሰቃቂው የሰው ዘር እልቂት ዳግም እንዳይከሰት በበይሎሩሲያ የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን እና የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን በጋራ ጸረ ሴማዊ ርእዮት የሚጻረር በሃይማኖቶች መካከል መከባበር የሚያጎላ ለማህብራዊ እና ሰብአዊ ሰላም ያቀና በሕንጸት መድረክ የተለያዩ ጥረቶች ይከናወናሉ፣ የክርስትናው እና የአይሁድ ሃይማኖት የሚያገናኙ ብዙ የእምነት አንቀጾች አሉ፣ ስለዚህ ይኸንን የጋራው የእምነት አንቀጽ በማጉላት የሚደረገው ውይይት ብዙ አወንታዊ ውጤት እያስገኘ ነው። ስለዚህ የቅዱሱ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የሮማው ሲናጎግ ጉብኝት የሃይማኖቶች የጋራው ውይይት ያለውን ክብር የሚያጎላ ወጣቱ ትውልድ በሰላም ባህል መታነጽ እንዳለበት የሚያሳስብ ሓዋርያዊ ምስክርነት ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.