2009-11-12 10:17:42

ሥነ ሕይወት ትኩረት የሰጠ ስብስባ ተፈጸመ ፡


ቫቲካን ውስጥ ሥነ ሕይወት በተመለከተ ቫቲካን ውስጥ ሲካሄድ የሰነበተው ስብስባ መፈጸሙ ተነግረዋል፡ ስብሰባው በየቫቲካን የሳይንስ ጳጳሳዊ ማእከል የተዘጋጀ መኖሩ የሚታወስ ነው።

ከተለያዩ ሀገራት የተውጥጡ የሳንስ ምሁራን በዚሁ ለአንድ ሳምንት የተካሄደው ስብሰባ ተሳታፊ መሆናችው የሚታወስ ሲሆን የዚሁ ስብሰባ ዋነኛ ዓላማ ከዚች ከምንኖርባት ዓለም ውጭ ሕይወት ያለባቸው ሌሎች ዓለማት እንዳሉ ለመዳሰስ መኖሩ የቫቲካን ይሳይንስ ጥናት ማእከል ዋና ዳይረክተር ኣአብ ኾሰ ፉነስ አስታውሰዋል ።

በዚሁ ስብሰባ ከተገኙ የሳይንስ ምሁራን በዩናይትድ ስቴትስ የአሪዞና ዩኒቨርሲቲ ፕሮፈሶር ክሪስ ኢምፐይ በፈረንሳ የሳይንስ ጥናት ዋና ሐላፊ ዶክቶር አተና ኩስተኒስ በጣልያን በሮማ በቶር ቨርጋታ ዩኒቨሲቲ የሥነ ፍጥረት ተማራማሪ ፕሮፈሶር ዮናታን ሉኒነ ይገኙባቸዋል ።

የዓለማችን ተመሳሳይነት ሕይወት ያላቸው ፕላነቶች ዓለማት መኖራቸው እና አለመኖራቸው ትኩረት ሰጥቶ በተካሀደው በዚሁ ስብሰባ በዚሁ አኳያ ቀደም ሲል የተካሄደው ስብሰባ አጋዥ መኖሩ ያመለክቱት ፕሮፈሶር ዮናታን ሉኒነ ከአስር ዓመታት በኃላ በተጨባጭ ለማወቅ ተስፋ እንዳለ ጠቁመው በፀሀይ ዙርያ ከሚገኙ ዘጠኝ ፕላነቶች በአራት ሕይወት የማስተናገድ ተክህሎ ሳይኖራቸው አይቀርም ተብሎ እንደሚጠረጠር አመልክተዋል።

የሳይንስ ጥናቱ እና ምርምር ቀጣይ መሆኑ እና ሥነ ሕይወት በተመለከተ በጣም ሩቅ ባልሆነ ግዜ አንድ አስደናቂ ግኝት ሳይኖር እንደማይቀርም የቫቲካን የሳይንስ ጥናት ማእከል ዳይረክተር የሳይንስ ምሁር አባ ኾሰ ፉነስ ገልጸዋል ።

በዩናይትድ ስቴትስ የአሪዞና ዩኒቨሲቲ ፕሮፈሶር ክሪስ ኢምፐይ ፡ ከአራት መቶ ዓመታት በፊት ጋሊለዮ ጋሊለይ የሰው ልጅ በጠፈር ላይ የነበረውን አመለካከት እንዲቀየር ማድረጉ አስታውሰው አሁን ባለው የተራቀቀ ተክኖሎጂ ባለፉት አስራ አምስት ዓመታት በፀሀይ ዙርያ ካሉ ፕላነቶች ሌላ ሌሎች አራት መቶ መኖራቸው ለመዋቅ መቻሉ እና ወደ ፊት በዚሁ ዘርፍ አስደናቂ ውጤቶች እንደሚገኙ አመልክተዋል ።

የሳይንስ ጥናቱ በተጠናከረ መልኩ ከሄደ የግኝቱ ግዜ አጭር እንደሚሆንም ፕሮፈሶሩ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል ።

በርካታ የሳይንስ ምሁራን ከዓለማችን ውጭ ሕይወት ያለው ፕላነት ዓለም መኖሩ አምነው ይህንኑ ለመለየት የሚያስችል ጥልቅ የሳይንስ ጥናት እየተካሄደ መሆኑንም ፕሮፈሶር ክሪስ ኢምፐይ መግለጻቸው ተነግረዋል ።

ኤውሮጳውያን ሰው የሚኖርበት የአሁኑ ሰሜን እና ላቲን አመሪካ መኖሩ ወድያውኑ ሳይሆን ግኝቱ ዘግይቶ መኖሩም አስታውሰዋል ።

ስለዚህ ቀስ በቀስ የሳይንስ ትምህርት የስው ልጅ ብዙ ነገር እንድያውቅ እና







All the contents on this site are copyrighted ©.