2009-11-11 14:43:33

ፊሊፒንስ


እ.ኤ.አ. ጥቅምት 11 ቀን 2009 ዓ.ም. በፊሊፒንስ ወንጌላዊ ላኡክ የአየር ላንድ ተወላጅ የቅዱስ ኮሎምቦስ ልኡካን ማህበር አባል አባ ሚካኤል ሲኖት መጠለፋቸው የሚዘከር ሲሆን፣ ካህኑን ነጻ ለማስለቀቅ ሲከናወን የነበረ ጥረት RealAudioMP3 ባለው ሳምንት ተከስቶ በነበረው ፖለቲካዊ መቃቃር ምክንያት ተቋርጦ በፊሊፒንስ መንግሥት እና ሚልፍ በመባል በሚጠራው የፊሊፒንስ የደቡብ ክልል ነጻ አውጭ እስላማዊ ግንባር መካከል ግኑኝነቱ ዳግም መጀመሩ ኤሺያን ኔውስ የዜና አገልግሎት ያረጋገጣል።

ይህ እስላማዊው የነጻነት ግንባር፣ አባ ሲኖት የተጠለፉበት ተብሎ በሚጠረጠረው በላኖአ አካባቢ ትላንትና 3 ሺሕ አባላቱን በማሰማራት ካህኑን ለመፈለግ እና ነጻ ለማስለቀቅ በሚደረገው ጥረት እየተሳተፉ መሆኑ ሲያስታውቅ፣ የፊሊፒንስ መንግሥት አባ ሲኖት የታገቱበት ክልል ተብለው በሚጠረጠሩት በሌሎች ሶስት ክልሎች የመከላከያ ኃይል አባላት ማሰማራቱ ትላትና አስታውቀዋል ሲል ሚስና የዜና አገልግሎት ገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.