2009-11-11 14:42:35

የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳስት ምክር ቤት


የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት 60ኛው ጉባኤው በአሲዚ የምክር ቤቱ ሊቀ መንበር የጀኖቫ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ባኛስኮ ባሰሙት ንግግር ተጀምሮ በመቀጠል ላይ ነው። ይህ ከትላትና በስትያ በአሲዚ ከተማ የተጀመረው RealAudioMP3 የኢጣልያው የብጹዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ስብሰባ በይፋ ያስጀመሩት ብፁዕ ካርዲናል ባኛስኮ፣ ለአፍሪቃ ትኵረት እንዲሰጥ እንዲሁም የካህናት የአገልግሎት ሚና እና በኢጣልያ በህዝባዊ አገልግሎት የተጠመዱት የፖለቲካ አካላት ኢጣሊያን ከማፍቀር መንፈስ የመነጨ አገልግሎት ይሰጡ ዘንድ በማሳሰብ፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ና ለጉባኤው ባስተላለፉት መልእክት የክርስትያን ሕብዝ እምነት ፍቅር እና ተስፋ ለማበረታታት የቤተ ክርስትያን እና የመንግሥት ግኑኝነት ለማጠናከር በማህበራዊ ባህል የወንጌል መንፈስ ለማስረጽ የብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤ እጅግ አስፈላጊ ነው እንዳሉም ብፁዕ ካርዲናል ባኛስኮ ባሰሙት ንግግር ጠቅሰውታል።

በቅሩቡ በሱዳን የተገደሉት ስድስት ክርስትያን ወንድማማቾች፣ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 25 ቀን 2009 ዓ.ም. የተጠናቀቀው የአፍሪቃ ብፁዕና ጳጳሳት ይፋዊው ሁለተኛ ሲኖዶስ፣ በአፍሪቃ ጎልቶ የሚይታየው ድኽነት እንዲቀረፍ ቢያስተጋባም፣ ከአለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን የተገባ ትኩረት ሳያገኝ መቀረቱ፣ ኵላዊት ቤተ ክርስትያን ወደ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ለመግባት በተደጋጋሚ ጥያቄ ያቀረቡት እና በማቅረብ ላይ የሚገኙት የአንግሊካን ጳጳሳት ካህናት እና ምእመናን በተመለከተ ቅዱስ ኣባታችን ር.ሊ.ጳ. ባለፈው ረቡዕ በይፋ ያወጁት ሓዋርያዊ ሕግ፣ ጠለቅ በማድረግ ብፁዕ ካርዲና ባኛስኮ ባሰሙት ንግግር በማብራራት፣ አክለውም ሕይወት እና ሞት በተመለከተ ያለውን ወቅታዊው ማኅበራዊ ሰብአዊ ባህል፣ ሞት የሕይወት ፍጻሜ እንደሆነ በመመልከት፣ የሞት ሓቅ ማየት የማይሻው በመስፋፋት ላይ ያለው ሞትን የሚደብቅ ለመርሳት የሚራወጥ ባህልን እና ሕይወትን ከልብ የማይል ያኗኗር ስልት የሚያስፋፋውን ባህል እግምት ውስጥ በማስገባት የኢጣሊያ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ያሳተመቸው አዲስ መጽሓፈ ግንዘት፣ በማስታወስ፣ የውሁዳን ባህል እና እምነት ማክበር ተገቢ ነው ሆኖም ግን ይከንን ተገቢ የሆነው ማህበራዊ ጉዳይ ተገን በማድረግ ኤውሮጳ እራሷን ባህል መርሳት የለባትም ካሉ በኋላ፣ በመጨረሻ ማንኛውም ዓይነት ከመጸነስ እስከ ባህራያዊ ሞት ሕይወት ላደጋ የሚያጋልጥ የሚቀናቀን በመስፋፋት ላይ ያለው የሞት ባህል በስነ ባህል መድረክ ተገቢ ምላሽ መስጠት ወሳኝ ነው ብለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.