2009-11-11 14:48:10

ቨነዝዋላ-ኮሎምቢያ


የቨነዝዋላ ርእሰ ብሔር ኡጎ ቻቨዝ ኮሎምቢያ ወታደራዊ ጥቃት የሰነዘረች እንደሆነ ለመከላከል እና አጸፋውን ለመመለስ የአገራቸው የመክላከያ ኃይል አባላት በተጠንቀቅ ላይ እንዲሆኑ ትእዛዝ ማስተላለፋቸው ሲገለጥ፣ RealAudioMP3 የኮሎምቢያው ርእሰ ብሔር ኡሪበ የርእሰ ብሔር ቻቨዝ ውሳኔ መሠረት የሌለው ነው በማለት ለተባበሩት የላቲን አሜሪካ አገሮች ማኅበር እና ለተባበሩት መንግሥታት የጸጥታ እና የደህንነት ምክር ቤት ጉዳዩ ግምት በመስጠት ውሳኔ ይሰጡበት ዘንድ አቤት እንደሚሉ አስታውቀዋል።

ርእሰ ብሔር ቻቨዝ በኮሎምቢያ እና በተባበሩት የአሜሪካ መንግሥታት መካከል የተደረሰው ወታደራዊ ስምምነት ተችተው እንደነበር የሚዝከር ሲሆን፣ በኢጣሊያ ማቸራታ በሚገኘው መንበረ ጥበብ የታሪክ መምህር የላቲን አሜሪካ ታሪክ ሊቅ ፕሮፈሶር ጀናሮ ካሮተኑቶ የኮሎምቢያም ሆነ የቨነዝዋላ ርእሰ ብሔራን የራሳቸው ፖለቲካዊ ጥቅም ላለ ማሰናከል የሚጠቅሙበት ስልት ነው እንጂ በትክክል ወታደራዊ ግጭት ይከስታል ብሎ ማመን አይቻልም ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.