2009-11-11 14:46:33

ሶማሊያ


በሶማሊያ ያለው የሰብአዊ ችግር በክልሉ ተከስቶ ባለው ኃይለኛው ዝናብ ባስከተለው የውኃ መጥለቅለቅ አደጋ ሳቢያ እጅግ መባባሱ ሲገለጥ፣ በተከስተወ የተፈጥሮ አደጋ ሳቢያ 16 ሺሕ ሕዝብ መፈናቀሉ ሚስና የዜና RealAudioMP3 አገልግሎት ያመለክታል።

የተባበሩት መግንሥታት በሶማሊያ የሰብአዊ እርዳታ አቀነባባሪ ጽ/ቤት፣ ተፈናቃዩ ሕዝብ በቤተ ዘመድ መጠለያ ማግኘቱ በማሳወቅ ባለፉት ቀናት ሁለት ያለም አቀፍ የምግብ ድርጅት ሠራተኞች መገደላቸው በመጥቀስ ለተጎዳው ሕዝብ አስፈላጊው እርዳታ ለማቅረብ በክልሉ ያለው ጸጥታ እና ደህንነት አስተማማኝ እንዳልሆነ እና ኃይለኛው ዝናብ የሶማሊያ ተፈናቃይ ህዝብ ወደ ሚገኝበት መጠለያ ሠፈር የምግብ እርዳታ ለማቀረብ ለሚደርገው ጥረት ተጨማሪ እንቅፋት መሆኑ አስታውቀዋል።

300 ሺሕ የሶማሊያ ተፈናቃይ ህዝብ በካኩማ እና ዳዳአብ ክልል በሚገኙት መጠለያ ሰፈር እንደሚገኝ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች እና የተፈናቃዮች የበላይ ድርጅት ሲያስታውቅ፣ በጠለያው ሠፈር በተከስተው ኃይለኛው ዝናብ ምክንያት በመጠለቅለቅ አደጋ መጠቃቱ እና ተፈናቃዩ ዝህብ ለተላላፊ አደገኛ በሽታ ጭምር መጋለጡ ድርጁት ያሰራጨው መገልጫ ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.