2009-11-09 14:00:23

የተባበሩት የአሜሪካ መንግሥታት


የተባበሩት የአሜሪካ መንግሥታት ርእሰ ብሔር ባራክ ኦባማ ጽኑ ፖሊቲካዊ ሰብአዊ ፍላጎት መሠረት በአገራቸው የጤና ጥበቃ ጉዳይ ያለውን አሠራር ሥር ነቀላዊ ለውጥ የሚያሰጠው ያረቀቁት አዲስ መመሪያ ከትላትና RealAudioMP3 በስቲያ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መጽደቁ ተገለጠ።

የዚህ አዲስ የአሜሪካ የጤና ጥበቃ ጉዳይ መመሪያ ለሁሉም የአሜሪካ ዜጎች የሚበጅ፣ በአገሪቱ እና ለአገሪቱ አዲስ ታሪካዊ ለውጥ መሆኑ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሊቀ መንበር ናንስይ ፐሎሲ ለጉባኤው ባሰሙት ንግግር ገልጠዋል። ይህ ውጤት ለርእሰ ብሔር ባራክ ኦባማ አቢይ ፖለቲካዊ ድል መሆኑ ሲገለጥ፣ ሰነዱ ለሕግ መወሰኛው የበላይ ምክር ቤት እንደሚቀርብ ለማወቅ ተችለዋል። ርእሰ ብሔር ኦባማ በዚህ ምክር ቤት ጭምር አዲሱ መመሪያ እንደሚጸድቅ ተስፋ እንዳላቸው በመግለጥ፣ ባንድ አመት ውስጥ እግብር ላይ እንደሚውል አልጠራጠርም ካሉ በኋላ ለሁሉም ለተባበሩት አሜሪካ መሥታት ሕዝብ ጥቅም የሚውል እና ማንም ከጤና እንክብካቤ የማግኘት መሠረታዊ መብት የተገለለ እንደማይሆን ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.