2009-11-09 14:01:39

የተባበሩት መንግሥታት


የተባበሩት መንግሥታት የተፈጥሮ የአካባቢ ጉዳይ ተጠሪ ይቮ ደ ቦኤር በስፐይን ባርቸሎና ከተማ ስለ የተፈጥሮ የአካባቢ ጉዳይ በተወያየው ጉባኤ ተሳትፎ መልስ እ.ኤ.አ. ከታህሳስ 7 ቀን እስከ ታህሳስ 18 በዴንማርክ ርእሰ ከተማ RealAudioMP3 የአየር ንብረት ጉዳይ እና ብከላ በሚል ርእሰ ጉዳይ ሊካሄድ ተወስኖ ያለው ዓለም አቀፍ ስብሰባ አቢይ ውጤት እንደሚያስገኝ አልጠራጥርም እንዳሉ ተገልጠዋል።

እ.ኤ.አ. እስከ 2020 ዓ.ም. ባለው የዓመታት ገደብ ውስጥ፣ በኢንዳስትሪ የበለጸጉት አገሮች በተፈጥሮ ያየር ንብረት ላይ የሚያስከትሉት ብከላ ለማጉደል እና በዚህ እቅድ በማደግ ላይ ያሉት አገሮች ጭምር እንዲሳተፉ የሚሰጡት እገዛ ጉዳይ በተመለከተ ባለፉት ሁለት የዓለም አቀፍ ጉባኤዎች የተገኙት አበይት ውጤቶች መሆናቸው አስታውሰው፣ ስለዚህ የዚህ አይነቱ ውሳኔ ለተፈጥሮ እና ለፍጥረት ኅልውና ወሳኝ ነው ብለዋል።

በኮፐንሃገን መንበረ ጥበብ መምህር የስነ ቅርጸ ምድር ሊቅ ሚኒክ ሮሲንግ፣ በመከሰት ላይ ያለው የአየር ንብረት መዛባት በዓለማችን የውኃ እጥረት እያስከተለ ነው፣ ስለዚህ ከወዲሁ ችግሩ ሳይባባስ የአየር ንብረት ጤንነት ለመንከባከብ እና ብከላ ለመቀነስ ተቀባይነት ያለው የልማት እቅድ እግብር ላይ ለማዋል ሁሉም ከዚህ ቀደም የተካሄዱት ስብሰባዎች ያጸድቁት ውሳኔዎች እግብር ላይ ማዋል በጣም አስፈላጊ ነው፣ ውሳኔ ማርቀቅ እና መቀበል ሳይሆን አንገብጋቢው ጉዳይ ውስኔዎችን እግብር ላይ ማዋል ነው ብለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.