2009-11-09 13:57:35

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ፣ ስፖርት የሕንጸት መድረክ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ዓለማውያን ምእመናን የሚንከባከበው ጳጳሳዊ ምክር ቤት፣ ቤተ ክርስትያን እና ስፖርት በሚል ርእሰ ጉዳይ ያነቃቃው እዚህ ሮማ በመካሄድ ላይ ላለው ጉባኤ ባስተላለፉት መልእክት፣ RealAudioMP3 ቤተ ክርስትያን የወጣቶች በስፖትር መሳተፍ በመደገፍ ስፖርት አወንታዊ ውደራ የሚታይበት መድረክ በግብረ ገብ የተካነ የሰብአዊ እና የመንፈሳዊ ሕንጸት የሚከናወንበት እሴቶች የሚያንጸባርቅ መሆን እንዳለበት በማሳሰብ፣ ስፖርት ሕንጸት እና እምነት ለካቶሊክ የስፖርት እንቅስቃሴ የማይነጣጠሉ ጉዳዮች ናቸው ብለዋል።

ስፖርት የሕንጸት ክፍል እንደሆነ በመረዳት በአወንታዊ ስሜት የሚከናወን እና ግብረ ገብ የሚከተል መሆን እንዳለበት ቅዱስነታቸው፣ በማሳሰብ በቁምስናዎች በትምህርት ቤቶች እና በስፖትር መኅበራት አማካኝነት ለወጣት የህብረተሰብ ክፍል የእሴቶች ሕንጸት ማስተላለፍ ተቀዳሚ እቅድ መሆን ይገባዋል ብለዋል። ስፖርት ለሰው ልጅ ለተሟላ እድገት የሚበጅ ጤናማ መሣሪያ መሆን አለበት ካሉ በኋላ በዚሁ መድረክ ካህናት ገዳማውያን እና ዓለማውያን ምእመናን የተገቡ አስተማሪዎች በመሆኑ ጤናማ ወጣት በማነጽ ረገድ አቢይ አስተአዋጽኦ መስጠት እንዳለባቸው በመግለጥ፣ ቤተ ክርስትያን ስፖርትን በመደገፍ አወንታዊ ፉክክር የሚታይበት እንዲሆን በማስተማር ሌላውን በስፖርት ዓለም እየተስፋፋ ያለው ኃይል ሰጭ ያደንዛዥ እጽዋት መጠቀም በሕይወት ላይ የሚያስከትለው ጉዳት በማብራራት፣ የካቶሊክ እምነት ተከታይ የሆኑት የስፖትር ጉዳይ መሪዎች እና አስልጣኞች እምነት እና ስፖትርን በማጣመር ወጣቱ የኅብረተሰብ ክፍል በሳል የሰብአዊ እድገት ይጎናጸፍ ዘንድ ማስልጠን እና ማነጽ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.