2009-11-06 14:21:00

የፊንዱፍ መጠለያ ሠፈር ስደተኛ ጉዳይ


ከአልጀርስ 1900 ኪሎ ሜትር በስተ ደቡባዊ ምዕራብ ባለው የቲንዱፍ የተፈናቃዮች እና ስደተኞች መጠለያ ሰፈር ውስጥ የሚገኙት ሳህራውያን ስደተኞች ጉዳይ እጅግ አሳሳቢ መሆኑ የሳህራዊ የግማሽ ጨረቃ የተራድኦ ማህበር RealAudioMP3 ሊቀ መንበር ያሂያ ቡሄሚያነ አስታወቁ።

እልባት ያጣው የተፈናቃይነት ሕይወት እና እንዲሁም ተከስቶ ያለው ዓለማዊው የኤኮኖሚው ቀውስ ምክንያት የሳሃራዊ ተፈናቃይ እና ስደተኛው ሕይወት ከቀን ወደ ቀን እጅግ እንዲበራታ ማድረጉ ቡሄሚያነ ገልጠው፣ እ.ኤ.አ. ከ 1970 ዓመተ ምህረት አጋማሽ በ ሞሮኮ እና በፖሊሳሪ ግንባር መካከል የተፈጠረው ግጭት ሳቢያ፣ ለሳሃራዊ ተፈናቃዮች እና ስደተኞች ብቸኛው መጠለያ የሆነው በቲንዱፍ ክልል የሚገኘው ሠፈር በአልጀሪያው ምድረ በዳ ክልል የሚገኝ በመሆኑም ለተፈናቃዩ ህዝብ ድጋፍ ለማቅረብ ሌላ ተጨማሪ እክል ሆኗል እንዳሉም ሚስና የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

ምንም’ኳ የተኩስ አቁም ስምምነት የጸና ቢሆንም ቅሉ፣ በፖሊሳሪ ግንባር እና በራባት መንግሥት መካከል ምንም ዓይነት ዘላቂነት ያለው ስምምን ባለ መደረሱ እርሱም የራባት መንግሥት የሳሃራ ምዕራባዊ ክልል ልኡላዊነቱን እውቅና ባለ መስጠቱ ምክንያት ውጥረት ባለበት እንዲጸና ማድረጉ ሲገለጥ፣ የተባበሩት መንግሥታት መገልጫ እንደሚያመለክተው ሳይሆን በታንዱፍ መጠለያ ሠፈር ውስጥ 165 ሺሕ ተፈናቃዮች እንዳሉ የፖሊሳሪ ግንባር መግለጫ ያመለክታል።







All the contents on this site are copyrighted ©.