2009-11-06 14:22:05

ቅዱስ ካርሎ ቦሮመዮ


የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ከትላትና በስትያ ቅዱስ ካሮሎ ቦሮመዮ አክብራ መዋሏ የሚታወስ ሲሆን፣ የዚህ ከቅዱስ አምብሮዚዮስ ጋር የሚላኖ ቅዱስ ጠባቂ በዓል ምክንያት የሚላኖ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል RealAudioMP3 ዲዮኒጂ ተታማንዚ ለካህናቶቻቸው ባስተላለፉት ምእዳን፣ ካህናት የጥሪያቸውን ስብአዊነት ገጹን ማሳወቅ ይኖርባቸዋል፣ የመረጡት የንጽሕና ሕይወት ያለው ክብር ዋጋ የጥሪያቸውን ሰብአዊነት ገጹን በማፈን የሚኖር ወይንም የሚከበር አይደለም በማለት፣ ንጽሕናን ወይንም ድንግልናን ለመኖር የጥሪ ሰብአዊ ገጽታውን ማጉላት ትልቅ መፍነሳዊ ፈውስ ነው እንዳሉ ሲር የዜና አገልግሎት ካሰራጨው የዜና ምንጭ ለመረዳት ተችለዋል።

ንጽሕና ስለ ፍቅር ጉዳይ በተመለከተ የሚደረገው ሕንጸት መሠረት ነው። በድንግልና መኖር የሚጠይቀው የክህነት ጥሪ፣ ሌላውን ለመሳብ እና ሰዎች ስለ ወንጌል ስለ ክርስትና ለመወያይየ እና ቀርቦ ለማወቅ እንዲችሉ የሚማርክ ኃይል ጭምር ነው። በንጽህና እና በድንግልና መኖር ጾታዊ ግኑኝነት ባለ ማድረግ የሚመሰከር ብቻ ሳይሆን በምትናገረው በአመለካከትህ ባቀራረብህ በጠቅላላ ከሌሎች ጋር እና ከራስህ ጋር ባለህ የተስተካከለ ግኑኝነት አማካኝነትም ይገለጣል እንዳሉ ሲር የዜና አገልግሎት አረጋገጠ።








All the contents on this site are copyrighted ©.