2009-11-06 14:18:39

ሓዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ለጎዳና ተዳዳሪዎች


15 የኤውሮጳ አገሮች ብጹዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ስለ ጎዳና ተዳዳሪዎች እና መንገደኞች ርእሰ ጉዳይ እ.ኤ.አ. ከጥቅምት 29 ቀን እስከ ህዳር 2 ቀን 2009 ዓ.ም. እዚህ በቫቲካን ሙያተኞች የተለያዩ የግብረ ሰናይ ማህበራት RealAudioMP3 እንዲሁም የደናግል እና የካህናት ማኅበራት ወካዮች ባሳተፈው ስብሰባው ለጎዳና ተዳዳሪዎች የሚሰጠው ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ መመሪያ አዘል አንድ የጋራ ሰነድ ማጽደቁ ተገለጠ።

ይህ የተካሄደው ስብሰባ ለጎዳና ተዳዳሪዎች እና ለመንገደኞች የሚሰጠው ሓዋርያዊ አገልግሎት እንዴት ባለ መልኩ መከናወን እንዳለበት በመወያየት፣ አርቆ ያጸደቀው ሰነድ መሆኑ ሲገለጥ፣ ሰነዱ የሁሉም ሰዎች ሰብአዊ መብት እና ፈቃድ እንዲሁም ሰብአዊ ክብር አለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እና ልዩነት መከበረ አለበት ከሚለው መሠረታዊ ሀሳብ በመነሳት፣ በነዚህ በ15 የኤውሮጳ አገሮች በጎዳና ለሚተዳደሩት የሚሰጠው ሓዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አገልግሎት በማቀናጀት እና በማዋሀድ ለማቅረብ የሚደግፍ መሆኑ ተገልጠዋል።

የተለያዩ የመጓጓዣ ስልት ለሚጠቀሙት በባቡርም ሆነ በአውራ ጎዳና ለሚጓዙት ቀርቦ ሓዋርያዊ አገልግሎት በመስጠት የሚያደርጉት ጉዞ ጥንቃቄ የተሞላው ለራሳቸውም ሆነ ለሌላው የአደጋ ጠንቅ እንዳይሆኑ ጉዞአቸው በኃላፊነት መንፈስ እንዲፈጽሙ ማነቃቃት እንደሚያስፈልግ፣ እንዲሁም በመንገዶች ዳር ቆመው ለክብር ሰራዥ ተግባር የሚዳረጉት፣ ተገደውም ሆነ በፈቃቸው በአመንዝራነት የሚተዳደሩት ቀርቦ በወንጌል መንፈስ የተመራ መንፈሳዊ ሰብአዊ እና ማኅበራዊ ሕንጸት ማቅረብ፣ ከወደቁበት ክብር ሰራዥ ተግባር ተላቀው ከማኅበርሰብ ጋር ተቀላቅለው ለመኖር እንዲችሉ እድል መፍጠር፣ ድኽነት እና የአመንዝራነት ሕይወት ምርጫ ጉዳይ በተመለከተ የጉባኤው ሰነድ እንደሚያመለክተው፣ ተፈላጊው የሚመረጠው ሕይወት ሳይሆን ከድኽነት መላቀቅ ነው የሚለው ይኽ አይነቱ የሕይወት ክብርነት ግድ ያማይለው ውሳኔ መርህ የሚያስከትለው ሰብአዊ ስቃይ ቀላል አለ መሆኑም ጉባኤው በማጤን፣ የሰው ልጅ ዕለታዊ እንጀራው አግኝቶ ሕይወቱን በክብር ይመራ ዘንድ እድል እንዲፈጠርለት በማሳሰብ፣ ሰው የሚከተለው መጥፎ ተግባር ከማውገዝ ይልቅ ለመጥፎ ተግባር የሚዳርገው ችግር መፍትሄ እንዲያገኝ የሚመለከተው አካል ኅሊና ማነቃቃት አስፈላጊ መሆኑም በሰነዱ ተመልክቷል።

ቤተ ክርስትያን ደህንነት እና ጸጥታ እንዲረጋገጥ ወዳጅህነት እንደራስህ ማፍቅር የሚለው እና ሰብአዊ ባህል ማነቃቃት በሰው ዘር መካከል ለአስፍሆተ ወንጌል ትልቅ እንቅፋት የሆነው፣ የመራራቅ የመጠራጠር የመሳሰሉት አጥሮች ማፍረስ ወሳኝ መሆኑ ሰነዱ ያመለክታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.