2009-11-04 13:32:45

የክህነት ዓመት


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ውሳኔ መሠረት ዘንድሮ የክህነት ዓመት እየተከበረ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፣ እዚህ ሮማ በሚገኘው ጳጳሳዊ የሳንታ ማሪያ ማጆረ ባሲሊካ የካህናት ጉዳይ የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር RealAudioMP3 ለካህነት ቅድስና በሚል ጠቅላይ መርሃ ግብረ መሠረት እያካሂደው ያለው መንፈሳዊ መርሃ ግብር እየቀጠለ መሆኑ ሲገለጥ፣ ይህ የቅዱስ ቁርባን እና የማርያማዊ መንፍሳዊነት ሰዓታት ነገ በሮማ ሰዓት አቆታጠር ልክ በ አራት ስዓት እንደሚከናወን ተገልጠዋል።

የካህናት ጉዳይ የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ማውሮ ፒያቸንሳ ያስተላለፉት መልእክት እንደሚያመለክተውም፣ ይህ የስነ ቤተ ክርስትያናዊነት እርሱም የጉባኤነት ባህይርይ የሚያረጋገጥ ዓመት መሆኑ በማብራራት፣ ኢየሱስ ና ተከተለኝ በማለት ለጠራው እና ለሚጠራዊ በክህነት ጥሪ ለሚኖረው ሁሉ በቅዱስ ቁርባን ፊት እና ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋር በመሆን እንዲጸለይ ምእመናንን የሚያነቃቃ የጸሎት መርሃ ግብር መሆኑም አብራርተዋል።

በዚህ የጸሎት መርሃ ግብር ሁሉም ምእመናን በተለይ ደግሞ ካህናት የዘርአ ክህነት ተማሪዎች ገዳማውያን እንዲሳተፉ ጥሪ በማቅረብ፣ በዚህ የጸሎት መርሃ ግብር በማኅበረሰብ ዘንድ የካህን መሠረታዊ አገልግሎት፣ ሁሉም በሚሥጢረ ጥምቀት አማካኝነት ለሁሉም የተሰጠው ጸጋ ጭምር እግምት ውስጥ በማስገባት ካህናታን በጸሎታችን እንድንደግፋቸው አደራ ብለዋል።

ይህ ነገ በሳንታ ማሪያ ማጆረ ባሲሊካ በቅዱስ ቁርባን ፊት የሚደረገው ያስተንትኖ ጸሎት ማርያም እና ሓዋርያት በጽርሃ ጽዮን ተሰብስበው የነበሩበትን ወቅት ሕያው የሚያደርግ እና የስብከተ ወንጌል ተልእኮ የሚያመለክት ነው ብለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.