2009-11-04 13:31:38

የስትራስበርግ ፍርድ ቤት ውሳኔ


የኤውሮጳ የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ጉዳይ የሚከታተለው ዋና ጽ/ቤቱ ስትራስበር የሚገኘው የበላይ ፍርድ ቤት እያንዳንዱ ቤተ ሰብ ልጁን እንደ የእምነቱ ለማነጽ ይችል ዘንድ RealAudioMP3 እና የማንም የሃይማኖት ነጻነት ላለመጣስ በሚል ምክንያት መስቀል በትምህርት ቤቶች ግድግዳ እንዳይሰቀል ውሳኔ መስጠቱ ተገለጠ።

ፍርድ ቤቱ አንዲት የኢጣሊያ ዜግነት ያላቸው አየር ላንድ ተወላጅ እናት በኢጣሊያ RealAudioMP3 ፓዶቫ ክፍለ ሃገር በሚገኘው በአባኖ ተርመ ከተማ ባለው ልጆቻቸው የሚማሩበት ተቋም ውስጥ በግድግዳ ተሰቅሎ የነበረው መስቀል በመቃወም መስቀሉ ይወርድ ዘንድ ያቀረቡት አቤቱታ በመቀበል ያስተላለፈው ውሳኔ ሲሆን፣ ፍርድ ቤት በዚህ ብቻ ሳይገታ የኢጣሊያ መንግሥት ክሱን ላቀረቡት እናት የግብረ ገብ ካሳ አምስት ሺሕ ኤውሮ ይከፍል ዘንድ ጭምር ሲበይን፣ የኢጣሊያ መንግሥት የፍር ቤቱ ውሳኔው ዳግም ይታይለት ዘንድ አቤት እንደሚል አስታውቀዋል።

የስትራስበርግ የኤውሮጳው የበላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ በማስመልከት የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቱ የካቶሊክ ትምህርት ጉዳይ የሚከታተለው ድርገት ሊቀ መንበር የተርኒ ናርኒ አመሊያ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቪንቸንዞ ፓሊያ፣ ከቫቲካን ረድዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ውሳኔው ሃይማኖታዊ ነክ ሳይሆን ካንድ ደካማ ስነ ሰብአዊነት ግንዛቤ የመነጨ ነው፣ ምክንያቱም ዓለማዊነት የሃይማኖት ምልክት አለ መኖር ማለት ሳይሆን፣ የሃይማኖት መግለጫ የሆኑትን የመቀበል እና የመደገፍ ብቃት ያለው ማለት ነው፣ ካልሆነ ግን የሃይማኖት መግለጫዎች ጨርሶ ማጥፋት የአስተሳሰብ እና የግንዛቤ ጠባብነት ነው የሚያመለክተው። ስለዚህ የነጻነት ባህል የሌላውን ባህል የሚቃወም የባዶነት መገልጫ ማለት አይደለም፣ ይህ ደግሞ ታሪክን እና ባህልን እንዲሁም ከጥንት ሲወርድ ሲዋረድ የመጣውን ባህል የሚቀናቀን አመለካከት ነው። አደባባዮቻችን መንገዶቻችን ያየን እንደሆነ የተለያዩ የመስቀል ምልክት ያለባቸው ሓውልቶች ንድፎች የስነ ጥበብ ባህል የስነ ሕንጻ ባህል የሚያንጸባርቅ ነው። ይህ የስነ ጥበብ ባህል የሌላውን ሃይማኖት ይወስናል ብሎ ሊያወድመው የሚያልም ማንም የለም። ር.ሊ.ጳ. ጳውሎስ ስድስተኛ በሮማ ከተማ አንድ መስጊድ ሊገነባ መሆኑ እንደሰሙ ትልቅ የስልጣኔ ምልክት ነው በማለት ነበር አስተያየት የሰጡት። ስለዚህ በትምህርት ቤት ውስጥ በግድግዳ የሚሰቀለው መስቀል ባስገዳጅ የራስህን ባህል በሌላው ላይ ማኖር የባህል ጫና ማድረግ ማለት አይደለም። በዚህ ባለንበት ዘመን ስንቱ ነው ተጨቁኖ መብቱ ተረግጦ በስቃይ ላይ የሚኖረው፣ ይህ መስቀል ለኛ ክርስትያኖች በተቀበልነው እምነት አንጻር ብቻ ሳይሆን እነዚህን የተዋረዱትን የተናቁትን የኅብረተሰባችን አባላትን ጭምር የሚያስታውሰን የላቀ የሰብአዊነት ምልክትም ጭምር ነው ይህ ደግሞ የላቀ የሰብአዊነት ትምህርት ለማስተላለፈ የሚረዳ ነው ብለዋል።

በሌላው ረገድ መስቀል የመለያ ምልክት ሲሆን፣ ቢሆንም የፍቅር ኵላዊነት አድማሱን የሚገልጥ አጥር ድንበር ጎሳ ዜግነት የማያግደው፣ ሁሉን ለሚያቅፍ ፍቅር መገልጫ ነው፣ ስለዚህ ለሁሉም የሚበጅ ምልክት ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.