2009-11-04 13:34:01

ህንድ


በህንድ የዛሬ አንድ ዓመት በፊት በትክክል ነሓሴ 25 ቀን 2008 ዓ.ም. በኦሪሳ ከተማ የተገደሉት የሂንዱ ሃይማኖት መሪ ላክሳማናንዳ ሳራዋቲ ለጸረ ክርስትያን ዓመጽ ምክንያት የሆነው የቀብር ሥነ ሥርዓት በመከናወን ላይ እያለ RealAudioMP3 አንድ ስለ ክርስትያኖች የሚሟገቱ የሂንዱ እምነት መንፍሳዊ መሪ መገደላቸው የሚዘከር ሲሆን፣ እኚህ የሂንዱ ሃይማኖት መንፈሳዊ መሪዎች ውስጥ አንዱ የሆኑት የሂንዱ ሃይማኖት የበላይ መንፈሳዊ መሪ ሳራዋቲ ቅትለት ተጠያቂ ማንነት የታወቀ ቢሆንም ቅሉ ክርስትያኖች ናቸው በሚል ሆን ተብሎ በአክራሪያን ሂንዱ የተጠነሰሰው ጸረ ክርስትያን አመጽ በመቃወም ክርስትያኖችን የተከላከሉ መሆናቸውም ይነግራል።

አክራሪያን የሂንዱ ሃይማኖት ተከታዮች በሰነዘሩት ጸረ ክርስትያን አመጽ የተደናገጡት ክርስትያን ምእመናን ቤታቸውን እና ንብረታቸውን በመተው መፈናቀላቸው፣ ብዙ ክርስትያን መእመናን ጭምር ለሞት መዳረጋቸው የሚዘከር ሲሆን፣ ከሂንዱ ሃይማኖት መሪዎች ውስጥ አንዱ የሆኑት ሲድሄስዋር ፕራድሃን ክርስትያኖች ላይ እየደረሰ የነበረው ግፍ እና በደል በመቃወም አንዳንድ የክልሉ ክርስትያኖች ካደጋ በማዳን ቤትን እና ንብረታቸው ጥለው እንዳይሸሹ ስለ ክርስትያኖች የተጣበቁት በዚህ ባሳዩት መልካም ተግባር የተቆጡ የሂንዱ አክራርያን እጅ ለሞት መዳረጋቸው የሚዘከር ሲሆን፣ በግድያው ተግባር የተጠረጠሩት የሂንዱ አክራርያን አባላት የካንድሃማል ፍርድ ቤት በደሙ ተጠያቂ አይደሉም ሲል ነጻ እንዲለቀቁ የሰጠው ፍርድ የክልሉ ክርስትያን ማህበረሰብ እጅግ እንዳሳዘነው ሲነገር፣ የህንድ የመላ ክርስትያን ምክር ቤት መሥራች እና የምክር ቤቱ ሊቀ መንበር ጆን ዳያ ፍርድ ቤት ውሳኔ ፍርደ ኢፍትሃዊነት ነው በማለት ቅሬታቸውን አሰምተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.