2009-11-02 12:40:25

የዓለማውያን ምእመናን ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት


ሙሊየሪስ ዲግኒታተም፣ የሴቶች ክብር በሚል ርእስ ሥር ር.ሊ.ጳ. የእግዚአብሔር አገልጋይ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግምዊ የደረስዋት ሓዋርያዊ መልእክት 20ኛው ዓመት መታሰቢያ ምክንያት በማድረግ ከ የካቲት 7 ቀን እስከ የካቲት 9 ቀን 2008 ዓ.ም. RealAudioMP3 የዓለማውያን ምእመናን ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ያካሄደው ዓለም አቀፍ ጉባኤ ያወታውን የማጠቃላያ ሰንድ ያካተተ፣ ሴት እና ወንድ፣ የሰብአዊነት ሙላት በሚል ርእስ ሥር አንድ መጽሓፍ ለሕትመት ማብቃቱ ዜኒት የዜና አገልግሎት ካሰራጨው ዜና ለማወቅ ተችለዋል።

ይህ በቫቲካን ማተሚያ ቤት የታተመው መጽሓፍ የመጀመሪያ ሕትመቱ በጣሊያንኛ ቋንቋ ሲሆን፣ በቅርቡ በስፓኒሽ በእንግሊዝኛ እና በፈረንሳይኛ ተተርጉሞ ለሕተመት እንደሚበቃ ዜኒት አስታወቀ። ስነ ሰብአዊ ጥናት መሠረት የሚገለጠው የሴት የሴትነት ባህርይ የሚያጎላ ከኅብረተሰብ እና ከባህል የሚሰጣት የተጽእኖ ባህርይ አንድ በአንድ በመለየት የሴት እውነተኛው ሴት በመሆንዋ ላይ ያለው የሴትነት ባህርያዋን የሚተነትን እና ሴተ እና ወንድ የስብአዊነት ሙላት መሆናቸው በሚገልጥ ሀሳብ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በቫቲካን እ.ኤ.አ. ከየካቲት 7 ቀን እስከ የካቲት 9 ቀን 2008 ዓ.ም. ተካሂዶ ለነበረው ዓውደ ጥናት፣ የክርስትያናውን ባህል አዲሱ ዘመን እና የስነ ምርምራ እድገት በማነጻጸር ባስተላለፉት መልእክት ያስተላለፉት ትምህርት ያካተተ ነው።

በተለያዩ ስለ ሰብአዊ ክብር ስለ ሴት እና ወንድ መብት እና ፈቃድ እንዲሁም ክብር ርእስ በማድረግ እ.ኤ.አ. በተካሄዱት በተለያዩ ዓለም አቀፍ ጉባኤዎች ይህ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ያስላለፈው ያቀረበው መልእክት እና መግለጫ ያካተተ መሆኑም ዜኒት ያረጋገጣል።

የዚህ መጽሓፍ መግቢያ የዓለማውያን ምእመናን ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ስታኒስላው ርይልኮ አማካኝነት የተጻፈ ሲሆን፣ በዚህ በምንኖርበት ዘመን ሴት እንዴት ባለ መልኵ እንደምትገለጥ በመተንተን ወንድ እና ሴት በመተባበር ቤተ ክርስትያን ቤተ ሰብ እና ኅበረተሰብን ለመገንባት የተጠሩ መሆናቸው በመተንተን፣ የማንነት መደናገር ለተለያዩ ችግሮች እንደሚያጋልጥ ሰፋ በማድረግ በማስረዳት፣ የሁሉም ሂደት መሠረት ለቅድስና መጠራት ሲሆን፣ ወንድ እና ሴት የሚፈጽሙት ሁሉ ለቅድስና መጠራታቸው ከማመን አኳያ የመነጨ መሆን እንዳለበት የሚገልጥ የመግቢያ መልእክት መሆኑ ዜኒት ያረጋገጣል።







All the contents on this site are copyrighted ©.