2009-11-02 12:41:26

የክህነት ዓመት፣ ወጣቱ ትውልድ ጥሪውን እንዲለይ መደገፍ


ዘንድሮ በመታሰብ ላይ ያለው የክህነት ዓመት ምክንያት የፊደይ ዶኑም ልኡካን ማኅበር አባል በጉዋተማላ ከ 30 ዓመት በላይ ይገለገሉ፣ ኣባ ኤኒዮ ቦሱ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃል ምልልስ፣ በጉዋተማላ በዘርአ ክህነት ትምህርት ቤት አለቃ በመሆን RealAudioMP3 ማገልገላቸው ጠቅሰው በአሁኑ ወቅት በቶሪኖ የትልቁ ዘርአ ክህነት ትምህርት ቤት አለቃ በመሆን ለክህነት የሚዘጋጁትን በመምራት ላይ እንደሚገኙ ገልጠው፣ ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ አባት እና መንፈሳዊ እናት በክህነት ጥሪ የሚኖሩ አገልጋይ አባት እና እናት በመሆን ሕዝበ እግዚአብሔርን መምራት ያለውን መርህ በማድረግ፣ እግዚአብሔር አባትም እናትም ነው፣ በርሱ ዘንድ የፍቅር ሙላት አለና፣ ስለዚህ ሁሉም በሕይወቱ የእግዚአብሔር እቅድ ለይቶ እንዲያውቅ በካህን አባትነት እና እናትነት መንፈስ ይመራል ይደገፋል፣ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን ሲጠራ ወዲያውኑ ሂዱ ወንጌልን ስበኩ ሳይል፣ ከርሱ ጋር እንዲቆዩ እና እንዲሆኑ እንዳሳሰባቸው ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የካህን ዓመት ምክንያት በማድረግ ያሰመሩበት ሀሳብ አባ ቦሱ በመዘከር በዘርአ ክህነት ትምህርት ቤት መኖር ከክርስቶስ እና ከተጠሩት ወንድሞች ጋር ወህደት የሚጸናበት የጸጋ ግዜ ነው ብለዋል።

የዘርአ ክህነት ትምህርት ቤት ዓመታት ክርስቶስ ከ 12 ደቀ መዛሙርቱ ጋር የኖረው ጊዜ እና ተመክሮ የሚያመለክት መሆኑንም አብራርተው፣ ደቀ መዛምርት ክርስቶስ ያደረገላቸው ሁሉ እርስ በእስራቸው በመመስከር እና በመኖር አለ እረኛ የቀሩት የደከሙትን ተስፋ የቆረጡትን ወደ ክርስቶስ ለማቅረብ የተጠሩ ናቸው፣ ስለዚህ ይኸንን በሚገባ ለመፈጸም ወደ ክርስቶስ ያቀረቡ መሆን አለባቸው፣ ስለዚህ የዘርአ ክህነት ትምህርት ቤት ዘመን ይኸንን ያሰማል ብለዋል።

ካህን የሰብአዊነት፣ የእግዚአብሔር ጉዳይ ሊቅ አለ ምንም ማፈግፈግ ለእግዚአብሔር መንግሥት መስፋፋት የሚያገለግል እራሱን ሳይቆጥብ በእግዚአብሔር ጉዳይ የሚጠመድ ማለት ነው፣ ስለዚህ ከዚህ አንጻር ሲታይ የክህነት ጥሪ የተቀበለ ሰው የክህነት ጥሪ ጥልቅ መንፈሳዊ እና ሰብአዊ ገጽታውን በሚገባ የተገነዘበ መሆን አለበት፣ ይኸንን ለማከናወን ቅድመ ዝግጅት የታደለም ነው ካሉ በኋላ፣ ካህን ወጣቱ ትውልድ ጥሪውን እንዲለይ የሚደገፍ ጸላይ አስተማሪ እና መንፈሳዊ መሪ ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.