2009-11-02 14:28:36

የሁሉም ቅዱሳን ዝክረ በዓል ተስታወሰ


የላቲን ሥርዓት አምልኮ የምትከተለው ቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ትናንት እሁድ የሁሉም ቅዱሳን በዓል አክብራ እና አስታውሳ መዋሏ ሲመለከት፣ ዛሬም የሁሉም ሙታን ዝክረ በዓል አክብራ መዋሏ ተገለጠ።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ትናንት እሁድ RealAudioMP3 በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ አደባባይ ላይ ከተሰበሰቡት አርባ ሺሕ ከሚገመቱት ምእመናን ጋር የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ከመድገማቸው በፊት የሁሉም ቅዱሳን በዓል ለክርስትያናዊ ሕይወታችን አግባብ የሌላቸውን ሁኔታዎ በመቃወም እና በትሕትና የፍቅር ፍጽምናን በመሻት አለምንም ስነ ልቦናዊ ችግር በቆራጥነት በደስታ የኢየሱስ ፈለግን ለመከተል ይጋብዘናል ሲሉ ገልጠው፣ ዛሬ ተስታውሶ የዋለውን የሁሉም ሙታን ምእመናን ዝክርረ በዓል ስናከብር የሙታኖቻችን ሥጋ የመጨረሻ ትንሣኤውን በመጠባበቅ ላይ በመበቃብር ውስጥ ማረፉን አውቀን መሆን አለበት ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.