2009-11-02 12:42:57

ሶማሊያ፣ የህዝብ መፈናቀል


በሶማሊያ መቋጫ ያጣው አመጽ እና ሁከት የአገሪቱ ህዝብ ለመፈናቀል እና ለተለያዩ ችግሮች እያጋለጠ መሆኑ፣ አገሪቱ እ.ኤ.አ. ከ 1991 ዓ.ም. አለ ማእከላዊ መንግሥት ከቀረችበት ዓመት ውዲህ በተደጋጋሚ የሚታይ መሆኑ ሲነገር፣ RealAudioMP3 ብዙ የአገሪቱ ዜጎች የኤደን ባህረ ሰላጤ በማቋረጥ ወደ የመን እንደሚሰደዱ ሲገለጥ፣ በዚህች ኢመንግሥታዊነት ሥርዓት በተስፋፋባት አገር የተለያያዩ የመንግሥት ያልሆኑ ያለም አቀፍ የተራድኦ ማኅበራት ለተጎዳው የሶማሊያ ህዝብ ድጋፍ ከማቅረብ እንዳልተቆጠቡ እና ይኽንን ጽናት እና ብርታትን የሚጠይቀው የተራድኦ ማኅብራት የሚሰጡት ድጋፍ ለማሰናከል የአገሪቱ አሸባርያ እና ጸንፈኞች ሙስሊሞች የተለያዩ እርምጃ እንደሚወስዱ እና ጥቃትም እንደሚጥሉ ይነገራል።

በምስራቅ አፍሪቃ በተለያዩ የሰብአዊ መርሃ ግብር የተሰማራው ትብብር እና ደጋፍ የሚያቀናብር ለምሥራቅ አፍሪቃ የተራድኦ ማህበር ሊቀ መንበር ማርኮ ሮተሊ፣ የሶማሊያ ተፈናቃይ ህዝብ 3 ሚሊዮን እንደሚገመት እና ከነዚህም ውስጥ አንድ ሚሊዮን ከግማሽ በአገሪቱ ውስጥ የሚገኝ ተፈናቃይ ያጠቃለለ መሆኑ ከቫቲካን ረድዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ገልጠው፣ በየመን ካራን በሚገኘው የተፈናቃዮች እና የስደተኞች መጠለያ ሰፈር ውስጥ 14 ሺሕ የሶማሊያ ዜጎች እንዳሉ ጠቅሰው ሌሎች በኤደን ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኘው ክልል ወደ 10 ሺሕ የሚገመቱ ተፈናቃዮች እንዳሉ በመጥቀስ በጠቅላላ 70 ሺሕ ይገመታሉ፣ ይህ ህዝብ እራሱን ለማዳን በአገሩ መቋጫ ያጣው የርስ በእርስ ግጭት ከሚያስከትልበት የሞት እና የመቁሰል አደጋ እራሱን ለማትረፍ የሚወስደው ውሳኔ ነው፣ በዚህች አገር ያለው ውጥረት እና ግጭት እስካልተፈታ ድረስ የህዝቡ መሰደድ ፈጽሞ እንደማያቋርጥ ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.