2009-10-30 14:21:09

ትላትና የአንጎል የደም ኡደት መቋረጥ ወይም የጸረ ኢክቱስ በሽታ ቀን ታስቦ ዋለ


በአንጎል የደም ኡደት መቋረጥ የሚያስከትለው በሽታ ቀን ትላትና ታስቦ መዋሉ ሲገለጥ፣ በዚህ በሽታ ሳቢያ በዓመት 6 ሚሊዮን ሕዝብ ለሞት አደጋ በየ 20 ሰከንድ አንድ ሰው በዚህ በሽታ እንደሚጠቃ እና በዓለም ብዙ ሕዝብ ለተለያዩ RealAudioMP3 የአእምሮ የአካል መሰናከል እና ለሽባነት የሚያጋልጥ ከመሆኑም አልፎ ለሞት ከሚዳርጉት ዋና ዋና በሽታዎች ተብለው ከሚጠቀሱት ውስጥ በሶስተኛ ደረጃ የሚገኝ መሆኑ ያለም አቀፍ የጤና ጥበቃ ድርጅት ከሰጠው መገለጫ ለመረዳት ተችለዋል።

ቀኑን ምክንያት በማድረግ ሮማ በሚገኘው የካቶሊክ የቅዱስ ልበ ኢየሱስ የሕክምና መንበረ ጥበብ ፕሮፈሶር ቪንቸንዞ ዲ ላዛሮ ከቫቲካን ረድዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ይህ በሽታ በአእምሮ ይደም ኡደት በመግታት የአንጎል አገልግሎት በማዛባት ለሽባነት በሽታ በማጋለጥ የመናገር የማየት ችግር የሚያስከትል መሆኑም ገልጠው፣ የስኳር በሽታ የደም መርጋት እንዲሁም ሲጋራ ማጨስ ለዚህ በሽታ የሚያጋልጥ ሲሆን፣ በአንግሎ የደም ሥር መቃወስ የሰውነት የደም ሥርጭት መዛባት የመሳሰሉት የጤና መታወክ ችግሮች የሚቀሰቅሱት እና ከዘር የሚዋረስም ነው ብለዋል።

በሽታውን ለመቆጣጠር እና የሚያስከትለው ጉዳት ለማስወገድ የሚደረገው ምርምር አመርቂ ውጤተ እያስገኘ መሆኑ ገልጠው፣ በበሽታው የተጠቃው ሰው ባስቸኳይ የሕክምና እርዳታ ካገኘ በሽታው የሚያስከትለው አቢይ ጉዳት ለመቆጣጠር ይቻላል፣ ሆኖም ግን ብዙዉን ጊዜ በትክክል በሽታው ለይቶ ካለ ማወቅ ወይንም የሰውነት መዝለፍለፍ ነው ተብሎ ስለ ሚታሰብ እና እንዲሁም የሕመም ስሜት የሌለው በመሆኑ ቸል ሲባል እየተባለ አስቸኳይ ሕክማ ካለ ማግኘት ሳቢያ ለሞት አደጋ የማጋለጥ ደረጃው ከፍ ብሎ ይገኛል፣ ከዚህ በሽታ ለመላቀቅ የሚስጠው ሕክምና ማስፋፋት እጅግ አስፈላጊ ነው ብለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.