2009-10-30 14:23:01

በደቡብ አፍሪቃ የጸረ ኤይድስ መርሃ ግብር


በደቡብ አፍሪቃ መንግሥት እና በአገሪቱ የሚገኙት አቢያተ ክርስትያን በጸረ ኤይድስ መርሃ ግብር የተዋጣለት ትብብር በማድረግ ላይ እንደሚገኙ የአቢያተ ክርስትያን መሪዎች እና የአገሪቱ የጤና ጥበቃ ሚኒ. አሮን ሞትሶአለዲ ባለፈው ማክሰኞ RealAudioMP3 በጉተንግ ከተማ ባካሄዱት ግኑኝነት አረጋግጠዋል።

ይህ የደቡብ አፍሪቃ ብሔራው የአቢያተ ክርስትያን መሪዎች መማክርት እና የጤና ጥበቃ ሚኒስትር በጋራ የጸረ ኤይድስ ዘመቻ ማካሄድ በሚል ውሳኔ መሠረት ባካሄዱት ግኑኝነት የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ሞትሶአለዲ ባሰሙት ንግግር፣ የኤይድስ በሽታ ደቡብ አፍሪቃን በእጅጉ እያጠቃ መሆኑ ገልጠው በአንዳንድ የአገሪቱ ከተሞች ከሚወለዱ ሕፃናት ውስጥ 45% በኤች አይ ቪ ቫይረስ የተለከፉ መሆናቸው እና በበሽታው የሚሞተውም ብዛት ከፍ እያለ መሆኑ ጠቅሰው፣ አቢያተ ክርስትያን ጸረ ኤይድስ ዘመቻ በማነቃቃት የሚሰጡት አገልግሎት በማድነቅ ሕዝቡ ስለ በሽታው በተመለከተ የሚሰጠው ሕንጸተ ይቀጥል ዘንድ አደራ እንዳሉም ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

በስብሰባው የተሳተፉት የደቡብ አፍሪቃ የፖሊስ ተጠሪ ቤኪ ቸለ የአገሪቱ መንግሥት የወንጀል ቡድኖችን ለመቆጣጠር እያራመደው ያለው ፖለቲካ አጥጋቢ ውጤተ እያስገኘ መሆኑም ጠቅሰው፣ ወላጆች፣ ማኅበርሰብም ጭምር ወንጀለኞች በማጋለጥ ሚና ይተባበሩ ዘንድ በማሳሰብ፣ በዚህች አገር የሚፈጸመው ወንጀል እንዲጎድል በማድረግ ሚና አቢያተ ክርስትያን የሚሰጡት የግብረ ገብ ሕንጸት እጅግ አስፈላጊ መሆኑ ቸለ ገልጠው፣ የቤተ ክርስትያን መሪዎች ከጤና ጥብቃ ሚኒስትር እና ከአገሪቱ የጸጥታ ኃይል ጎን በመሆን ጤናማ ዜጋ በመመሥረት መርሃ ግብር የሚስጡት አስተዋጽኦ የሚመሰገን ነው እንዳሉ ፊደስ የዜና አገግሎት አስታውቀዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.