2009-10-30 14:27:10

ሞዛምቢክ፣ ሕዝባዊ ምርጫ


በሞዛምቢክ ከ 10 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ የተሳተፈበት ሕዝባዊ ምርጫ ከትላትና በስትያ መካሄዱ ሲገለጥ፣ የአገሪቱ ርእሰ ብሔር ለመሆን በእጩነት የቀረቡት የርእሰ ብሔር ሥልጣን ተልእኮ ያጠናቀቁት ዳግም ለምርጫ የቀረቡት የሶሻሊዝም ርእዮት RealAudioMP3 ተከታይ የሞዛምቢክ ብሔራዊ የነጻነት ግንባር የፖለቲካ ሰልፍ መሪ ርእሰ ብሔር አርማንዶ ጉኤቡዛ፣ የሞዛምቢክ ብሔራዊ ንቅናቄ የወግ አጥባቂ ርእዮት የሚያንጸባርቅ የፖሊቲካ ሰልፍ መሪ አልፎንሶ ድሃላካማ እና የሞዛምቢክ ዴሞክራሲያዊ እንቅስቃሴ መሪ ቤይራ ዛቪዝ ሲማንጎ መሆናቸውም ታውቀዋል።

የምርጫው ተቆጣጣሪ ድርገት ሊቀ መንበር ዥዋው ሌፓልዶ ኮስታ የምርጫው ሂደት የተረጋጋ ግልጽ እና ያልተጭበረበረ ነበር ሲሉ፣ የአገሪቱ ኖቲሲያስ የተሰየመው እለታዊ ጋዜጣ እንዳመለከተውም በዚህ በተባካሄደው ምርጫ የሕዝብ ተሳትፎ እ.ኤ.አ. በ 2004 ዓ.ም. ተካሂደው ከነበረው ምርጫ እጅግ ከፍ ያለ መሆኑ በመግለጥ፣ የምርጫው ውጤት እ.ኤ.አ. ህዳር 12 ቀን 2009 ዓ.ም. በይፋ እንደሚገለጥም አስታውቀዋል።

የማፑቱ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ፍራንሲስኮ ቺሞዮ የምርጫው መርሃ ግብር መሠረት በማድረግ ባስተላለፉት ሓዋርያዊ መልእክት፣ በምርጫው መሳተፍ ለአገር ግንባታ እና እድገት መቆም ማለት መሆኑ ገልጠው የአገር ዕጣ ዕድል ህዝብ ነው እንዳሉም ለማወቅ ተችለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.