2009-10-30 14:19:07

ሜዲትራኒያን የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ለተነፈጋቸው ባሕር


እዚህ ሮማ በሚገኘው ጳጳሳዊ ግረጎሪያኖ መንበረ ጥበብ ትላትና ስለ ስደተኞች ጉዳይ በተወያየው ዓለም አቀፍ ጉባኤ ተገኝተው ንግግር ያሰሙት የስደተኞች እና የተጓዦች ሓዋርያዊ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ አጎስቲኖ ማርኬቶ፣ RealAudioMP3 ከተለያዩ ችግሮች እራሳቸውን ለማላቀቅ የሚሰደዱት ምንም’ኳ የሕገ ወጥ ስደተኞች ተብለው ቢገለጡም ቅሉ የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ውሳኔ ሊከበርላቸው ይገባል ብለዋል።

የሜዲትራኒያን ባሕር በማቋረጥ የሚሰደዱት የሕገ ወጥ ስደተኞች የሚያከናወኑት የተስፋ ጸዓት ለመግታት የሚደረገው ኃይለኛ ቁጥጥር፣ በሰው እና በሕይወት ላይ አቢይ ጉዳት እያስከተለ መሆኑ በማብራራት፣ እ.ኤ.አ. የ 1951 ዓ.ም. የጄነቭ የሰው ልጅ መብት እና ፈቃድ ውሳኔ እንዲሁም ስለ ተፈናቃዮች እና የፖለቲካ ጥገኞች ጉዳይ በተመለከተ እ.ኤ.አ. በ 1967 ዓ.ም. የተደነገገው ያለም አቀፍ ውሳኔ እንዲሁም በ1990 ዓ.ም. የዱብሊን ውሳኔ መሠረት ማንም ሕልውናው ለአደጋ የተጋለጠ ስደተኛ ሊባረር እና ወደ መጣበት ሊሽኝ እንደማይገባው የተገለጠ ቢሆንም ቅሉ፣ ይህ ውሳኔ ብዙውን ጊዜ ሲጣስ ይታያል፣ ለስደት የሚዳርገው ምክንያት ሳይጣራ ከሊቢያ የተነሱት ስደተኞች በመጥቀስ ከኢጣሊያው ወደ ሊቢያ የሚሸኙት ስደተኞች በሊቢያ በሚገኙት መጠለያ ሰፈር እንዲቆዩ ቢደረጉም፣ ለተለያዩ ሰብአዊ አደጋ እንደሚጋለጡ ገልጠው፣ ምክንያቱም ሊቢያ የ1951 ዓ.ም. የጄነቭ ውሳኔ እና እንዲሁም የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች እና የተፈናቃዮች የበላይ ድርገት ጭምር እውቅና ያልሰጠች አገር ነች፣ ስለዚህ ይኸንን ውሳኔ ወደ ማያከብሩ አገሮች ስደተኛው መሸኘት ጸረ ሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ነው ብለዋል። ከተለያዩ የሰብአዊ መብት ረገጣዎች እራሳቸውን ለማዳን የሚሰደዱት ወደ መጡበት የመሸኘቱ ውሳኔ በምንም ተአምር ምክንያታዊ ሊሆን አይችልም እንዳሉም ተገልጠዋል።

ይህ በንዲህ እንዳለም ባለፈው ማክሰኞ በኢጣልያ የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን በካሪታስ የሚጠራው የተራድኦ ማኅበር ቅርንጫፍ በኢጣሊያ የሚኖሩት ስደተኞች ጉዳይ በተመለከተ ባወጣው የአኃዝ ሰነድ፣ ስደተኛው ለኢጣሊያ እና በኢጣሊያ ትልቅ ሃብት መሆኑ ተሠምሮበት ይገኛል።








All the contents on this site are copyrighted ©.