2009-10-28 14:14:14

ፖሊቲካዊ ቀውስ በዚምባብዌ


በዚምባብዌ በተመሠረተው የብሔራዊ አንድነት መንግሥት መካከል የተከሰተው አለ መግባባት ለማስወገድ በመካሄድ ላይ ያሉት ጥረቶች በተለይ ደግሞ ከትላትና በስትያ ለአራት ሰዓት የተካሄደው ውይይት አለ ምንም RealAudioMP3 ስምምነት መበተኑ ተገልጠዋል።

ይህ የዚምባብዌ የአገራዊው አንድነት መንግሥት ከተቋቋመበት እለት ጀምሮ ምንም አይነት ውስጠ ስምምነት እንዳለነብረው ቢገለጥም ቅሉ፣ ይኽንን ችግር ለመፍታት በዚህች አገር እ.ኤ.አ. ከ 1980 ዓ.ም. ጀምረው በሥልጣን ላይ ያሉት ርእሰ ብሔር ሮበርት ሙጋቤ እና እ.ኤ.አ. መጋቢት 23 ቀን 2008 ዓ.ም. ተካሂዶ በነበረው ሕዝባዊ ምርጫ ያብላጫ ድምጽ ባለ ቤት የሆነው የተቃዋሚው የፖለቲካ ሰልፍ መሪ ሞርጋን ዝቫንጊራይ የተሳተፉበት ግኑኝነት እንደነበር ሲገለጥ፣ ዝቫንጊራይ ብሔራዊው የአገር አንድነት መንግሥት ያከተመለት ነው በማለት መግለጫ ሰጥተው እንደነበር የሚታወስ ሲሆን፣ በዚህ በያዝነው ሳምንት ማብቂያ አንድ ልዩ እና አስቸኳይ ስብሰባ ሊካሄድ መሆኑ ከሃራሬ የሚሰራጩ ዜናዎች ይጠቁማሉ።








All the contents on this site are copyrighted ©.