2009-10-28 14:12:00

የሕንጸት መሠረቶች፣ ምርምር፣ ሃይማኖት እና ፍቅር


የቨነዚያ ፓትሪያርክ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ስኮላ ሮማ የሚገኘው ከተመሠረተ 60ኛው ዓመቱ ያገባደደው ጳጳሳዊ የሳሊዚያን መንበረ ጥበብ የትምህር ዘመን መክፈቻ የቀረበው መሥዋዕተ ቅዳሴ በመምራት ይህ ጳጳሳዊ መንበረ ጥበብ ለባህል RealAudioMP3 እድገት የሰጠው አስተዋጽኦ አቢይ መሆኑ ባሰሙት ስብከት በማስታወስ፣ የእውነት ምክንያታዊ ጸጋነቱን ለይቶ ለማወቅ እና ለመኖር እንዲቻል የሚደገፍ መንበረ ጥበብ ነው ብለዋል። መናብረተ ጥበብ የሰው ልጅ ሰብአዊነቱን ለማረጋገጥ ተሚከተለውን መንገድ የሚመለከትበት ነው፣ ስለዚህ ከዚህ አንኳያ የአስተማሪዎች ኃላፊነት እጅግ ከፍተኛ መሆኑ ለመረዳትም እንደማይዳግትም ገልጠው፣ አስተማሪዎች እውነትን ለመመስከር የተጠሩ ተማሪዎች ጸጋ ከሆነው ከተጫባጩ ዓለም ጋር እንዲገናኙ ለማድረግ የሚጠመዱ ናቸው ብለዋል።

ዶን ቦስኮ፣ የሕንጸት መሠረት የሚላቸውን ምርምር ሃይማኖት እና ፍቅር አንድ በአንድ በማብራራት፣ እነዚህ ሦስቱ የሕንጸት መሠረቶች የማይነጣጠሉ መሆናቸው እና የሰው ልጅ ለማወቅ የሚጓጓ ይህ ደግሞ እውነትን ለማወቅ የተጠራ እና የተገናኘው እውነት ለሌሎች ለማካፈልም ፍላጎት ያለው ፍጡር መሆኑ እንደሚያረጋግጥ ሰፋ በማድረግ አስረድተዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.