2009-10-28 14:10:57

ብፁዕ ካርዲናል ኤርዶ፣ ስለ ሁለተኛው የአፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ


እ.ኤ.አ. ከጥቅምት 4 ቀን 2009 ዓ.ም. እስከ ጥቅምት 25 ቀን 2009 ዓ.ም. እዚህ በቫቲካን የተካሄደው ልዩ የአፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት ሁለተኛው ሲኖዶስ በማስመልከት በሲኖዶሱ የተሳተፉት የኤውሮጳ ብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤዎች ህብረት RealAudioMP3 ሊቀ መንበር፣ የኤስተርጎም እና ቡዳፐስት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ፐተር ኤርዶ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ገምገሚ መግለጫ መስጠታቸው ተገለጠ።

ይህ ሁለተኛው የአፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ተስፋ የጎላበት የመንፈስ ቅዱስ ድጋፍ እና ኃይል የተገለጠበት እንደነበርም በመጥቀስ፣ የአፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት እርቅ ፍትሕ እና ሰላም በዚህች ክፍለ ዓለም እንዲረጋገጥ ያላሰለሰ መንፈሳዊ ሰብአዊ ጥረት ለማድረግ ቆረጠው በመነሳት ያከናወኑት ውይይት የሚደነቅ ነው ካሉ በኋላ፣ የሰው ልጅ ከእግዚአብሔር ጋር ያለው ግኑኝነት መሠረት ካላደረገ በስተቀረ እርቅ ፍትሕ እና ሰላም ለማረጋገጥ ይቅር እና ማለሙም ፈጽሞ የማይቻል መሆኑ የመሰከረ ሲኖዶስ ነበር ብለዋል።

አለ የእግዚአብሔር ምህረት እርቅ ፍትህ እና ሰላም እንደማይኖርም ብፁዕ ካርዲናል ፐተር ኦርዶ ገልጠው የአፍሪቃ ብፁዓን የሲኖዶስ አበው ባካሄዱት የሃሳብ ልውውጥ መስክረዋል። በአፍሪቃ ካቶሊካዊት እና በኤውሮጳ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን መካከል ያለው ሁለናመዊ ትብብር በማብራራት፣ ይኽንን ግኑኝነት የሚያጠናክሩ እና የሚመሩ የኤውሮጳ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት እና ከአፍሪቃ እና ማዳጋስካር የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የተወጣጡ ድርገቶች መቋቋማቸውንም አስታውሰው፣ የአፍሪቃ ይፋዊው ሁለተኛ ሲኖዶስ ይኸንን ግኑኝነት እቢይ ግምት እንደሰጠበትም ገልጠው፣ ግኑኝነቱ በቁምስናዎች እና በሰበካዎች ስለ ስደተኞች ጉዳይ ስለ የካህናት ሕንጸት በመሳሰሉት ዘርፎች የሚገለጥ ነው ብለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.