2009-10-27 13:48:08

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ.፣ እርቅ ፍትሕ እና ሰላም ገቢራዊ ለማድረግ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በተገኙበት እዚህ በቫቲካን እ.ኤ.አ. ከጥቅምት 4 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ ሲካሄድ የሰነበተው አፍሪቃ የራሷ ዕጣ እድል ግንባር ቀደም ተወናያን እና ባለ ቤት ትሆን ዘንድ ያሳሰበው ይፋዊው ሁለተኛው የአፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ መጠናቀቁ ሲገለጥ፣ ቅዱስነታቸው ቅዳሜ በቀረበው የምሳ ግብዣ ተገኝተው ለብፁዓን የሲኖዶስ አበው RealAudioMP3 ባሰሙት ንግግር፣ ብፁዓን የሲኖዶስ አበው ያካሄዱት ሲኖዶስ የሚመሰገን እና የተዋጣለት እንደነበርን ገልጠው፣ ይህ እርቅ ፍትሕ እና ሰላም በሚል ጠቅላይ ርእስ ተመርቶ የተካሄደው ሁለተኛው የአፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ፣ እንዲከናወን ለፈቀደው በመንፈስ ቅዱስ ድጋፍ ቃሉን እና ፈቃዱን በማዳመጥ ወደ ውህደት በሚመራው መንገድ ለመጓዝ እንድንችል ላደረገው አስጀምሮ ላስጨረሰን እግዚአብሔር ምስጋና ይገባዋል ካሉ በኋላ፣ ቤተ ክርስትያን የእግዚአብሔር ቤተ ሰብ የሚል የተሰጣት መግለጫ፣ ጽንሰ ሀሳብ ወይን የሩቅ ግብ ሳይሆን ሕያው ገጠመኝ መሆኑ፣ ይህ እንደ እግዚአብሔር ቤተሰብ በአንድነት ብፁዓን አበው በመገናኘት ያካሄዱት ሁለተኛው የአፍርቃ ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ምስክር ነው ብለዋል።

እርቅ ፍትሕ እና ሰላም በሚል ርእስ ሥር የተካሄደው ሲኖዶስ፣ ፖሊቲካዊ መልክ ወይንም ደግሞ መንፈሳዊ ገጽታው ብቻ የሚያንጸባር ባንዱ ገጽታ ብቻ የታጠረ ሳይሆን ሁለቱን ገጽታዎች ሚዛኑ በጠበቀ ሂደት አሳክቶ መከናወኑ ጠቅሰው፣ የሲኖዱ ጠቅላይ ርእስ አቢይ ፖለቲካዊ ገጽታ ያለው ቢሆንም ነገር ግን እርቅ ፍትሕ እና ሰላም አለ ጥልቅ የልብ መንጻት፣ ባልታደሰ እና ባልተለወጠ አመለካከት እንዲሁም ከእግዚአብሔር ጋር ግኑኝነት ካልተደረገ ፈጽሞ የማይጨበጥ ባዶ ሃሳብ መሆኑ አስረድተው፣ ስለዚህ እርቅ ፍትህ እና ሰላም ለማረጋገጥ ትክክለኛ እና ተጨባጭ ፖለቲካዊ ሂደት እና ጥልቅ መንፍሳዊነትን ይጠይቃል ብለዋል። ብፁዓን የሲኖዶስ አበው ያላቸውን የእረኝነት ጥሪ ወደ ጎን በማድረግ የፖለቲካ አካላትን ቀስረው፣ የፖለቲካ ኃላፊነት የቤተ ክርስትያን እንደሆነ የሚያስመስል ውይይት አላካሄዱም ብለዋል።

ስለዚህ የተካሄደው ሲኖዶስ ፖለቲካ የሚያንጸባርቅ የፖሊቲካ መድረክ እንዳልነበረም ገልጠው፣ በሌላው ረገድ ከተጨባጩ ዓለም የተገለለ መንፈሳዊ ገጽታ ብቻ ያጎላ፣ ከተጨባጩ ዓለም የተነጠለ፣ እንዳልነበረም ጠቅሰው፣ እረኞች ተጨባጩን ዓለም በእግዚአብሔር አስተያየት እና እቅድ እንዲሁም በእግዚአብሔር ቃል ተመርተው በመዳሰስ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያንጸባርቁ ናቸው ካሉ በኋላ፣ ስለዚህ እረኞች ከተጨባጩ ዓለም ሳይገለሉ ተጨባጩን ዓለም በማንበብ፣ ሕዝበ እግዚአብሔርን እንደ እግዚአብሔር ቃል የሚመሩ ናቸው፣ ስለዚህ ጥልቅ መንፈሳውያን ሊሆኑ ይገባቸዋል ብለዋል። ፖለቲካዊ መፍትሔ በማፈላለግ፣ ፖለቲካዊ መንገድ የሚያመለክቱ ሳይሆን የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያንጸባርቁ ሕዝበ እግዚአብሔርን በእግዚአብሔር ፈቃድ የሚመሩ መሆን ይገባቸዋል።

እግዚአብሔርም የተመሰገነ ይሁን፣ ይህ የተካሄደው ሲኖዶስ ይኸንን ያጎላ ነበር በማለት። ሲኖዶስ ማለት የጋራ ጉዞ ወይንም የጋራ ሂደት ማለት መሆኑ አስረድተው፣ ይኸንን የጋራ ሂደት በመከተል አብረን ወደ እግዚአብሔር እንጓዝ በራችንን ለእግዚአብሔር እንክፈትለት በመካከላችን መንግሥቱ ያኖር ዘንድ ዓለም በሮቹን ለእግዚአብሔር ይከፍት ዘንድ የእግዚአብሔር መንገድ አመልካቾች እንሁን በማለት ምእዳን ሰጥተው ንግግራቸውን እንዳጠቃለሉ ከቅድስት መንበር የተላለፈልን ዜና ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.