2009-10-23 15:02:36

የሲኖዶስ አበው ልኡካን ከኢጣሊያው የውጭ ጉዳይ ሚኒ. ጋር ተገናኙ


ሁለተኛው ይፋዊው የአፍሪቃ ብፁዓን አበው ሲኖዶስ ልኡካን ትላትና ከኢጣሊያው የውጭ ጉዳይ ሚኒ. ፍራንኮ ፍራቲኒ ጋር መገናኘታቸው የሲኖዶስ የዜና እና የማስታወቂያ ቢሮ ካሰራጨው ዜና ለማወቅ ሲቻል፣ ለአፍሪቃ እድግት እንዲሁም RealAudioMP3 በአፍሪቃ የሚከሰቱት ጸረ ክርስትያን አመጽ እና የዘመኑ ባርነት ተብለው ለሚገለጡት ለተለያዩ ክብር ሰራዥ ተግባሮችን የሚዳርጉት ሰዎችን ከቦታ ቦታ የማዘዋወር ድርጊት፣ የጦር መሣሪያ መስፋፋት የመሳሰሉትን የአፍሪቃ ህዝብ እጅግ ላደጋ እያጋለጡ ያሉት እና ተመሳሳይ ተግባሮች ለማስወገድ፣ በኢጣሊያ እና በአፍሪቃ ካቶሊክ አቢያተ ክርስትያን መካከል የሚደረገውን ትብብር ለማሳየል ምን መደረግ እንዳለበት መወያየታቸው ተገልጠዋል። በአፍሪቃ እርቅ ፍትሕ እና ሰላም እውን ለማድረግ ሰውን ማእከል ያደረገ ፖለቲካ ማረማመድ ዓለማዊነት ትሥሥር የሚያስከትለው ጉዳት በተለይ ደግሞ በጠና ድኽነት የሚገኙት የኅብረተሰብ አባላት የማግለሉ አዝማሚያ ማስወገድ ወሳኝ መሆኑ በተካሂደው ግኑኝነት ተሰምሮበታል።

የሲኖዶስ ብፁዓን አበው ልኡካን የመሩት ብፁዕ ካርዲናል ፍርንሲስ አሪንዘ የተካሄደው ግኑኝነት አወንታዊ እና የአመለካከት ውኅደት የተረጋገጠበት ነበር ሲሉ፣ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ገልጠው፣ ወደ ኢጣሊያ ለከፍተኛ ትምህርት የሚላኩ የአፍሪቃ ውሉደ ክኅነት አባላት እና የዘርአ ክህነት ተማሪዎች በየሁለት ዓመት የመኖሪያ ፈቃዳቸው ለማሳደስ የሚደረገው አሠራር ብዙ ችግር እያስከተለ መሆኑ በማስመልከት፣ ይህ ዓይነቱ አሠራር ተወግዶ ለትምህርት እስከ ሚቆዩበት የጊዜ ገደብ የሚያገለግል የመኖሪያ ፈቃድ ያገኙ ዘንድ ብፁዓን አበው ለውጭ ጉዳይ ሚኒ. ፍራንኮ ፍራቲኒ ሃሳብ ማቅረባቸው ገልጠው፣ ከዚህ ጋር በማያያዝም በተለያዩ ችግሮች ተገደው ወደ ኢጣሊያ በጠቅላላ ወደ ኤውሮጳ የሚገቡት የአፍሪቃ ስደተኞች ለመቆጣጠር የኤውሮጳ አገሮች የስደተኛ ማስተዳደሪያ ደንብ ሊኖራቸው ግድ ነው፣ ሆኖም ግን የሚደነገጉት ሕጎች ሰውን ማእከል ያደረገ፣ የስደተኛው ችግር እግምት ውስጥ የሚያስገባ እንዲሆን፣ ብጹዓን የሲኖዶስ አበው ልኡካን ማሳሰባቸው ብፁዕ ካርዲናል አሪንዘ ገልጠው፣ ወደ ኤውሮጳ ለመሰደድ የአፍሪቃ በረሃማው ክልል እንዲሁም የሜዲትራኒያን ባህር ለማቋርጥ የሚያደርገው ጉዞ እጅግ አሰቃቂ እና ለሞት የሚዳርግ መሆኑም ዘክረው፣ ሕይወቱን ለማሻሻል ሰብአዊ መብት እና ፈቃድ እንዲከበርለት የሚጠይቀው ሰው፣ አትሰደድ ለማለት አይቻልም። ሲሉ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒ. ፍራንኮ ፍራቲኒ በበኵላቸውም ስለ ተካሄደው ግኑኝነት አስመልክተው ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የኢጣሊያ መንግሥት ለአፍሪቃ ልማት፣ በዚህች ክፍለ አለም እርቅ ፍትሕ እና ሰላም ለማረጋገጥ በሚደረጉት ጥረቶች ተቀዳሚው ሚና እንደሚጫወትም ጠቅሰው፣ በአፍሪቃ የሃይማኖት ነጻነት እንዲከበር ይህ ጉዳይ በተመለከተም ኢጣልያ ብቻ ሳትሆን በኤውሮጳ ደረጃ ቆራጥ ውሳኔ እንዲሰጠው መንግሥታቸው ስለዙሁ ጉዳይ አቢይ ቅስቀሳ እያካሄደ መሆኑም ገልጠው፣ የአፍሪቃ ወጣት በተለያዩ የሙያ ዘርፍ ለማሰልጠን የመንበረ ጥበብ ብቃት በአፍሪቃ እንዲያይል የትምህርት እድል ለማስፋፋት ኢጣሊያ አበክራ እንደምትሠራ በመጥቀስ፣ የዓለማችን መጪው ብሩህ ዕድል አፍሪቃ ነች ሲሉ የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.