2009-10-23 14:59:43

ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ሹመት ሰጡ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ስለ ቤተሰብ ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት እና የፍትህ እና የሰላም ጳጳሳዊ ምክር ቤት እንዲመሩ ሁለት አዲስ ዋና ጸሓፍት RealAudioMP3 መሾማቸው ተገለጠ።

57 ዓመት ዕድሜ ያላቸው የፈረንሳይ ተወላጅ የአማኑኤል ማኅበርሰብ ኣባል በጳጳሳዊ የስነ ሕይወት ተቋም ምክትል ሊቀ መንበር በመሆን በማገልገል ላይ ያሉት ብፁዕ አቡነ ዣን ላፊተ ስለ ቤተሰብ ጉዳይ የሚከታተለው ምክር ቤት በዋና ጸሃፊነት እንዲመሩ፣ እንዲሁም 59 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ብፁዕ አቡነ ማሪዮ ቶሶ በአማካሪነት የሚያገለግሉበት ጳጳሳዊ የፍትሕ እና የሰላም ምክር ቤት ዋና ጸሃፊ ሆነው እንዲመሩ በቅዱስ አብታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ መሾማቸው የቅድስት መንበር መገልጫ ያመለክታል።

ይህ በንእንዲህ እንዳለም በዴሞክራሲያዊት ሬፓብሊክ ኮንጎ የቡድጃላ ሰበካ ሊቀ ጳጳስ በመሆን በማገልገል ላይ ያሉት ብፁዕ አቡነ ጆሴፍ ቢላንጂ ኤግዋንጋ ኤዲባ ታሳመ የቤተ ክርስትያን ሕግ አንቀጽ 401 ቍጥር 2 መሠረት በማድረግ በእድሜ ገደብ ምክንያት ኃላፊነታቸውን ለማስረከብ ያቀረቡት ጥያቄ ር.ሊ.ጳ. በነዲትክቶስ 16ኛ እንደተቀበሉት የቅድስት መንበር መገልጫ ያረጋገጣል።








All the contents on this site are copyrighted ©.