2009-10-23 15:01:06

ሁለተኛው ይፋዊው የአፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ


እርቅ ፍትሕ እና ሰላም በሚል ዋና ርእስ ተመርቶ በመካሄድ ላይ ያለው የአፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ወደ ፍጻሜው በመቃረብ ላይ መሆኑ ሲነገር፣ ትላትና በ18ኛው ቀነ ጉባኤውን፣ በሚቀጥሉት ቀናት ድምጸ ውሳኔ የሚሰጥበት በይፋ የቀረበው RealAudioMP3 የማጠቃለያ ሰነድ በማስደገፍ ዝግ ውይይት ማካሄዱ የሲኖዶስ የግኑኝነት እና የማስታወቂያ ጉዳይ ጽ/ቤት ካሰራጨው ዜና ለማወቅ ተችለዋል።

ይህ ጰራቅሊጦስ የሚል መጠሪያ የተሰጠው የአፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ትላንትና ባካሄደው ዝግ ስብሰባ፣ በአፍሪቃ በመስፋፋት ላይ ያለው ምድረ በዳነት፣ የደን ሃብት ምንጠራ እያስከተለው ያለው ችግር፣ በጠቅላላ ስለ ያካባቢ ተፈጥሮ ጉዳይ በማስደገፍ ሰፊ ውይይት ማካሄዱ ተረጋገጠዋል። በዚህ አጋጣሚም የዲሞክራሲው ሥርዓት ለማረጋገጥ እስቸጋሪ በሆነው ጎዳና በመራመድ ላይ በምተግኘው ካሜሩን የባሜዳ ከተማ ሊቀ ጳጳስ ብፅዕ አቡነ ኮርነሊዩስ ፎንተም ኤሱዋ ከቫቲካን ሬዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የአፍሪቃ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ድምጿን ከፍ በማድረግ ሙስናን በማውገዝ ጸረ ሙስና ያነጣጠረ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ማነቃቃት ይኖርባታል ብለዋል።

ይህ የብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ፣ የአፍሪቃ ቤተ ክርስትያን ከባቢሎናዊነት ተላቃ ጴራቅሊጦሳዊነትን ያረጋገጠችበት መሆኑ ገልጠው፣ የአፍሪቃ ቤተ ክርስትያን ጉዳይ፣ ወንጌል መሠረት በማድረግ የዚህች ክፍለ ዓለም ሰብአዊ ማኅበራዊ ፖለቲካዊ ኤኮኖሚያዊ ችግሮችን ቀርቦ ለመመከት ያገዘ ትልቅ ጸጋ ነው ብለዋል።

በአፍሪቃ የሚታዩት ዘርፈ ብዙ ችግሮች ለመቅረፈ ወጣቱ የኅብረተሰብ ክፍል ማነጽ የሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ተቀዳሚ እቅድ መሆን እንዳለበትም አሳስበው፣ ወጣት ማነጽ ያፍሪቃን ብሩህ ተስፋ መቀስቀስ ማለት መሆኑም ገልጠው፣ እርቅ ፍትህ እና ሰላም ለማርረጋገጥ የሚደረገው ጉዞ በቁርጥ ፍቃድ መታደስ እና መለወጥን የሚጠይቅ መሆኑ በማብራራት የአፍሪቃን እና የሕዝቧን ጥቅም የሚያስቀድሙ ያመራር አካላት የሚያስፈልጋት መሆኗንም አብራርተው፣ አፍሪቃ የተፈጥሮ ሃብቷ የመንከባከብ ባህል ጭምር ማጎልበት ይኖርባታል ሲሉ የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.