2009-10-19 13:25:31

የአፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ፣ የማጠቃለያ ሰነድ ንድፍ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲቶኮስ 16ኛ በተገኙበት እዚህ በቫቲካን እርቅ ፍትህ እና ሰላም በሚል ዋና ርእስ ተመርቶ በመካሄድ ላይ ያለው ሁለተኛው የአፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ የሲኖዶስ ጠቅላይ ዋና ጸሓፊ በመመርመር ቅደም ተከተል RealAudioMP3 በማስያዝ እፊታችን ዓርብ የሲኖዶስ ብፁዓን አበው ድምጽ እንዲሰጡበት ለጉባኤ ውሳኔ የሚቀርበውን የማጠቃለያ ሰነድ ንድፍ በማቅረብ የሁለተኛው ሳምንት ጉባኤው ባለፈው ቅዳሜ ማጠናቀቁ ተገልጠዋል።

የሲኖዶስ የማጠቃለያው ሰነድ ንድፍ፣ ተስፋን ያጎላ የሰው ልብ የሚቀሰቅስ ለአፍሪቃ ሕዝብ መንፈሳዊ ምግብ መሆኑ ሲገለጥ፣ ይህ በእንግሊዝኛ በጣልያንኛ በፈረንሳይኛ እና በፖርቱጋል ቋንቋ የቀረበው የማጠቃለያው ንድፈ ሰነድ፣ የሰላም የፍትሕ እና የእርቅ አስፈላጊነቱን የሚያጎላ እና እነዚህ ወሳኝ እሴቶች ከቤተሰብ የሴቶች መብት እና ፈቃድ ከማክበር የፖለቲካው ዓለም ለማኅበራዊ እና ለአገር ጥቅም ያቀና ከማድረግ የሕጻናት መብት እና ፈቃድ ከማክበር የተፈጥሮ ሃብት እና የአካባቢ ጥበቃ ከመንከባከብ እና የኤኮኖሚ ስነ ምግባር ለማረጋገጥ የቤተ ክርስትያን ማኅበራዊ ትምህርት መሠረት ከማድረግ የሚጀመር መሆኑ የተመለከተበት ነው።

ዓለማውያን ምእመናን በቤተ ክርስትያን የነቃ ተሳትፎ እንዲኖራቸው፣ የአፍሪቃ ቤተ ክርስትያን 60% ለሚወክሉዋት ወጣቶች የተገባ ሕንጸት ማቅረብ፣ በተለያዩ አገሮች የሚገኙት ያፍሪቃ ስደተኞች ጉዳይ፣ በተለያዩ አገሮች በሓዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ተሰማርተው የሚገኙት አፍሪቃውያን ልኡካን ወንጌል ለአፍሪቃ ትልቅ ሃብት መናቸው የተገለጠበት ሰነድ መሆኑ ሲገለጥ፣ አፍሪቃን አንቆ ወደ ኋላ እያስቀራት ያለው የጸረ ሰላም መሠረት የሆነው ድኽነት፣ ሕዝቦችን እያሰቃየ ያለው ቀዛፊው የኤይድስ በሽታ ለማስወገድ እና ብሎም በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል የጋራው ውይይት እንዲሁም በአቢያተ ክርስትያን ለአንድነት ያቀና የጋራው ግኑኝነት ኅብረት ኃይል መሆኑ በማመን ለውህደት አቢይ ጥማት ባለው መንፈስ እንዲመራም ሰነዱ ያስገነዝባል።







All the contents on this site are copyrighted ©.